የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w11 6/1 ገጽ 18
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በኢየሱስ ላይ ሞት የፈረደበት ሊቀ ካህን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ኢየሱስ ወደ ሐና ከዚያም ወደ ቀያፋ ተወሰደ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ወደ ሐና ከዚያም ወደ ቀያፋ ተወሰደ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ጴጥሮስ ኢየሱስን ካደው
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
w11 6/1 ገጽ 18

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ሐዋርያው ጴጥሮስ ወደ ቆርኔሌዎስ እንዲሄድ ከመታዘዙ በፊት በቆዳ ፋቂው ቤት አርፎ እንደነበር መጠቀሱ የሚያስተላልፈው የተለየ መልእክት አለ?

▪ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ የሰፈረው ዘገባ ጴጥሮስ “በኢዮጴ ስምዖን ከተባለ አንድ ቆዳ ፋቂ ጋር ለበርካታ ቀናት” እንደተቀመጠ ይገልጻል፤ ስምዖን “ቤቱ በባሕሩ አጠገብ” ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 9:43፤ 10:6) ቆዳ መፋቅ በአይሁዳውያን ዘንድ ርኩስና የተናቀ ሥራ እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠር ነበር። የአይሁዳውያን ታልሙድ ቆዳ መፋቅ አዛባ ከመዛቅ ይበልጥ የተናቀ ሥራ እንደሆነ ይገልጻል። ስምዖን የሚሠራው ሥራ በአብዛኛው የእንስሳ በድን እንዲነካ የሚያስገድደው ሲሆን ይህም ስምዖንን በሕጉ መሠረት ሁልጊዜ ርኩስ እንዲሆን ያደርገው ነበር። (ዘሌዋውያን 5:2፤ 11:39) ስምዖን ሥራውን ለማከናወን የባሕር ውኃ ተጠቅሞ ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁሙ አንዳንድ መረጃዎች አሉ፤ እንዲሁም ቆዳ የመፋቅ ሥራ “መጥፎ ሽታ” የሚፈጥር ከመሆኑ አንጻር የስምዖን ቤት የሚገኘው በከተማው ዳርቻ ላይ ሳይሆን እንደማይቀር የተለያዩ መረጃዎች ይገልጻሉ።

ያም ሆኖ ጴጥሮስ፣ ስምዖን ጋር ለማረፍ ፈቃደኛ ሆኗል። ይህ ሁኔታ ከጴጥሮስ በፊት የነበረው ኢየሱስ ለሰዎች ጭፍን ጥላቻ እንዳልነበረው ሁሉ ጴጥሮስም በአይሁዳውያን ዘንድ በስፋት የሚታየው ዝንባሌ ይኸውም ርኩስ እንደሆኑ ተደርገው ለሚታሰቡ ሰዎች ጭፍን ጥላቻ የማሳደር ዝንባሌ ተገቢ አለመሆኑን ተገንዝቦ ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁም ነው።​—ማቴዎስ 9:11፤ ሉቃስ 7:36-50

ኢየሱስ “አንተው ራስህ ተናገርከው” ሲል ምን ማለቱ ነበር?

▪ የአይሁድ ሊቀ ካህናት የነበረው ቀያፋ ኢየሱስን በእርግጥ እሱ ክርስቶስ ማለትም የአምላክ ልጅ መሆን አለመሆኑን በግልጽ እንዲናገር በጠየቀው ጊዜ ኢየሱስ “አንተው ራስህ ተናገርከው” የሚል መልስ ሰጥቶ ነበር። (ማቴዎስ 26:63, 64) ታዲያ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ምን ማለቱ ነበር?

ኢየሱስ እንዲህ ሲል የቀያፋን ጥያቄ አድበስብሶ ለማለፍ መሞከሩ አልነበረም። “አንተው ራስህ ተናገርከው” የሚለው አባባል አንድ ነገር እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ አይሁዳውያን የሚጠቀሙበት የተለመደ ዘይቤያዊ አነጋገር ሳይሆን አይቀርም። ለምሳሌ ያህል፣ የኢየሩሳሌም ታልሙድ በመባል የሚታወቀው በአራተኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. የተዘጋጀው የአይሁድ ሃይማኖታዊ ጽሑፍ አንድ አይሁዳዊ ስለ አንድ ረቢ መሞት በተጠየቀ ጊዜ “አንተው ተናገርከው” ብሎ እንደመለሰ ይገልጻል። ይህ አባባል ግለሰቡ ረቢው ስለመሞቱ የሰጠው ማረጋገጫ ነበር።

ኢየሱስ ሊቀ ካህናቱ አንድ ሰው እውነቱን እንዲናገር የማስማል ሥልጣን እንዳለው ተገንዝቦ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ዝም ማለቱ ክርስቶስ መሆኑን እንደ መካድ ሊቆጠርበት ይችላል። በመሆኑም ኢየሱስ “አንተው ራስህ ተናገርከው” በማለት መልስ መስጠቱ ሊቀ ካህናቱ የተናገረው ነገር ትክክል መሆኑን የሚያረጋግጥ ነበር። ማርቆስ በጻፈው ተመሳሳይ ዘገባ ላይ እንደተገለጸው ኢየሱስ እሱ በእርግጥ መሲሕ ስለመሆኑ ቀያፋ ላቀረበለት ቀጥተኛ ጥያቄ “አዎን ነኝ” የሚል ድፍረት የተሞላበት መልስ ሰጥቷል።​—ማርቆስ 14:62፤ በተጨማሪም ማቴዎስ 26:25⁠ን እና ማርቆስ 15:2⁠ን ተመልከት።

[በገጽ 18 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በፊዝ፣ ሞሮኮ ያለ አንድ የቆዳ መፋቂያ ቦታ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ