መዝሙር 44
በመከሩ ሥራ በደስታ መካፈል
በወረቀት የሚታተመው
1. ያለነው በመከር ወራት ነው፤
ይህ ለኛ ታላቅ ክብር ነው።
አጫጆች ቢሆኑም መላእክት፣
እኛም አለን ድርሻና መብት።
ኢየሱስ ሥራውን በመሥራት፣
መልካም ምሳሌያችን ሆኗል።
ያገኘነው መብት እጅግ ታላቅ ነው፤
በደስታ እንፈጽመው።
2. ለአምላክ፣ ለሰው ያለን ፍቅር፣
እንድንተጋ ግድ ይለናል።
የመከር ሥራው አስቸኳይ ነው፤
የመጨረሻው ቀን ቀርቧል።
ከአምላክ ጋር አብረን ስንሠራ
ወደር የለውም ደስታችን።
አምላክ በሰጠን ሥራ ከጸናን
በረከት እናገኛለን።