መዝሙር 109
የይሖዋን በኩር አወድሱ
በወረቀት የሚታተመው
1. ይክበር ያምላክ በኩር፤
ይሖዋ ’ምላክ ሾሞታል።
በረከትን ያፈሳል፤
እውነት፣ ፍትሕ ያሰፍናል።
ክብር ግርማ ተላብሷል፤
ላምላክ ስም ይቀናል።
ያሳውቃል ይሖዋን፣
ሉዓላዊነቱን።
(አዝማች)
ይክበር ያምላክ በኩር!
ሊወደስ ይገባዋል፤
ከጽዮን ተራራ ላይ
አሁን መግዛት ጀምሯል።
2. ይክበር ያምላክ በኩር፤
ለኛ ሲል ሞቶልናል።
ትሑት ነው ቤዛ ከፍሏል፤
ኃጢያታችን ይሻራል።
ብቅ አለች በነጭ አምራ፣
የጌታ ሙሽራ።
ይህ የሰማይ ጋብቻ፣
ነው ለጽድቅ ማስረጃ።
(አዝማች)
ይክበር ያምላክ በኩር!
ሊወደስ ይገባዋል፤
ከጽዮን ተራራ ላይ
አሁን መግዛት ጀምሯል።