መዝሙር 57
በልቤ የማሰላስለው ነገር
በወረቀት የሚታተመው
1. በልቤ ’ማሰላስለው፣
ቀኑን ሙሉ የማስበው፣
ደስ ያሰኝህ ፈጣሪዬ፤
በቃልህ ያጽናኝ ጌታዬ።
ችግር፣ ሐሳብ ሲያስጨንቀኝ፣
ሌሊት እንቅልፌን ሲነሳኝ፣
ያኔ ስላንተ ላውጠንጥን፤
ቀና ሐሳብ እንዲኖረኝ።
2. ንጹሕ፣ እውነት የሆነውን፣
በጎ ነገር ያለበትን፣
ስለነዚህ ማሰብ ሁሌ፣
ሰላም ’ሚሰጥ ይሁን ለኔ።
አንተ ሐሳብህ ድንቅ ነው፤
ቁጥሩስ ምንኛ ብዙ ነው!
ይህን አሰላስላለሁ፤
ትኩረቴም በነዚህ ላይ ነው።
(በተጨማሪም መዝ. 49:3፤ 63:6፤ 139:17, 23ን፣ ፊልጵ. 4:7, 8ን እና 1 ጢሞ. 4:15ን ተመልከት።)