መዝሙር 72
ፍቅርን ማዳበር
በወረቀት የሚታተመው
1. ወደ አምላክ እንጸልያለን፤
ባሕርያቱን እንዲያላብሰን።
በተለይ ከሁሉም ’ሚልቀው፣
የመንፈሱ ውጤት ፍቅር ነው።
ችሎታ፣ ጥበብ፣ ድፍረት ኖሮን፣
ፍቅር ባይኖረን ከንቱዎች ነን።
የማይከስም ፍቅር ካዳበርን፣
ጸንተን እሱን ’ናስደስታለን።
2. ሁሌም ስናስተምር ሰዎችን፣
ምን ሊጠቅመን እውቀት ብቻውን!
ያምላክን ቃል ስንመግባቸው፣
ፍቅርን በተግባር ’ናሳያቸው።
እንችላለን ችግር፣ መከራ፣
ፍቅራችን ከሆነ ጠንካራ።
ምንም ዓይነት ችግር ቢገጥመን፣
ፍቅር አይከስምም ያልፋል ሁሉን።
(በተጨማሪም ዮሐ. 21:17ን፣ 1 ቆሮ. 13:13ን እና ገላ. 6:2ን ተመልከት።)