መዝሙር 108
ይሖዋን ስለ መንግሥቱ አወድሱት
በወረቀት የሚታተመው
(ራእይ 21:2)
1. በሁሉ ላይ እንዲገዛ
ይሖዋ ልጁን ሾሟል፤
ምድር ላይ ፈቃዱ እንዲሆን
ዙፋኑ በፍትሕ ጸንቷል።
(አዝማች)
ያህ ልጁን ሾሟል አወድሱት፤
ት’ዛዙን የምትፈጽሙ።
በየ’ለቱ የምትከተሉት፣
ኢየሱስን ከፍ አ’ርጉት።
ያህ ልጁን ሾሟል አወድሱት፤
አንግሦታል አመስግኑት።
ያምላክን ቅዱስ ስም እንዲያስከብር፣
ቀብቶታል በክብር።
2. የክርስቶስ ውድ ወንድሞች፣
እንዳዲስ ተወለዱ።
ድርሻ አላቸው በመንግሥቱ፤
ምድርን ገነት ያደርጋሉ።
(አዝማች)
ያህ ልጁን ሾሟል አወድሱት፤
ት’ዛዙን የምትፈጽሙ።
በየ’ለቱ የምትከተሉት፣
ኢየሱስን ከፍ አ’ርጉት።
ያህ ልጁን ሾሟል አወድሱት፤
አንግሦታል አመስግኑት።
ያምላክን ቅዱስ ስም እንዲያስከብር፣
ቀብቶታል በክብር።
(በተጨማሪም ምሳሌ 29:4ን፣ ኢሳ. 66:7, 8ን፣ ዮሐ. 10:4ን እና ራእይ 5:9, 10ን ተመልከት።)