መዝሙር 62
የማን ንብረት ነን?
በወረቀት የሚታተመው
(ሮም 14:8)
1. የማን ነኝ ትላለህ?
ለማን ትታዘዛለህ?
ልትገዛለት የመረጥከው
ጌታህና አምላክህ ነው።
ለሁለት አማልክት
ልብን ከፍሎ በመስጠት፣
ሁለቱን መውደድ ስለማይቻል
መወሰን ይገባሃል።
2. የማን ነኝ ትላለህ?
ማንን ትታዘዛለህ?
አንደኛው እውነት ሌላው ሐሰት
ናቸውና አንዱን ምረጥ።
ታማኝ የምትሆነው
ለዚህ ዓለም ቄሳር ነው?
ወይስ ለእውነተኛው አምላክህ
ዘወትር ትገዛለህ?
3. እኔ የምሆነው
የይሖዋ ንብረት ነው።
በሰማይ ላለው ውድ አባቴ
እፈጽማለሁ ስ’ለቴን።
በዋጋ ገዝቶኛል፤
ታማኝ ልሆን ይገባል።
ቤዛ አድርጎ ሰጥቶኛል ልጁን፤
አወድሳለሁ ስሙን።
(በተጨማሪም ኢያሱ 24:15ን፣ መዝ. 116:14, 18ን እና 2 ጢሞ. 2:19ን ተመልከት።)