መዝሙር 48
በየዕለቱ ከይሖዋ ጋር መሄድ
በወረቀት የሚታተመው
(ሚክያስ 6:8)
1. አባታችን መብቱን ሰጠን፤
እጁን ይዘን ለመሄድ አብረን።
ታማኝ ፍቅሩ ወደር የለው፤
ጎዳናውን ለሚፈልግ ሰው።
መንገዱን አመቻቸልን፤
አብረነው መሄድ ቻልን።
ራሳችንን ወስነናል፤
ከይሖዋ ጎን ቆመናል።
2. ባለንበት የፍርድ ቀን፣
መጨረሻው በቀረበበት፣
መከራ ይደርስብናል፤
ከባድ ስደት ያጋጥመናል።
አምላክ ግን ይጠብቀናል፤
እሱን መያዝ ይበጃል።
እናምልከው ለዘላለም፤
ታማኝ በመሆን ምንጊዜም።
3. አምላካችን ይረዳናል፤
በመንፈሱ፣ በቃሉ በኩል።
በጉባኤም ያንጸናል፤
የበጎቹን ጸሎት ይሰማል።
አይተወንም በጉዟችን፣
እንዳንስት መንገዱን፣
ደግነቱን እንድንመስል፣
ትሑት መሆን እንድንችል።
(በተጨማሪም ዘፍ. 5:24፤ 6:9ን እና 1 ነገ. 2:3, 4ን ተመልከት።)