መዝሙር 112
ታላቁ አምላክ ይሖዋ
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ አምላክ አንተ ታላቅ ነህ፤
ውዳሴ ይገባሃል፤
ትክክል ነው መንገድህ።
ታላቅ ዙፋንህ ጸንቷል በፍትሕ፤
የዘላለም አምላክ ነህ።
2. ኃጢያት፣ በደልን ይቅር የምትል፤
እንዳንተ ’ሚምሩትን
በነፃ የምትምር።
ፍትሐዊ ንጉሥ ደግም እንደሆንክ
በሥራህ የምታሳይ።
3. ሰዎች፣ መላእክት አንተን ያክብሩህ፤
ይቀደስ ታላቅ ስምህ።
ማንም አያምፅብህ።
ቶሎ ምድር ላይ ፈቃድህን ያ’ርግ፣
የሰማዩ መንግሥትህ።