መዝሙር 70
‘ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለይታችሁ እወቁ’
በወረቀት የሚታተመው
1. ለመለየት እውነት የሆነውን፣
ለመለየት መልካሙን፣
ለማወቅ ይበልጥ አስፈላጊውን፣
ይገባናል ማስተዋል!
ክፉን ጥላ፤ ውደድ ጥሩን።
ደስታ አለው አምላክን መፍራት።
በጸሎት ጽና፤
ቃሉን አጥና፤
ወሳኝ ነገሮች ናቸውና።
2. የመንግሥቱን ምሥራች ከመስበክ፣
በጎችን ከመፈለግ፣
ወዳምላክ ከመምራት የተሻለ፣
ሌላ ምን ሥራ አለ?
መስማት፣ ማወቅ አለባቸው።
እንርዳቸው፤
ፍቅርን በተግባር እናሳያቸው፤
ነፃ ይውጡ!
ትልቅ ዋጋ አለው ስብከቱ።
3. አስፈላጊ ነገር ላይ ካተኮርን፣
በእምነት እንጸናለን።
ውስጣዊ ሰላም እናገኛለን፤
ተስፋው ይሆናል እውን።
የልብ ወዳጅ ይኖረናል፤
ፍቅርም ያድጋል።
መቅደም ያለበትን ካስቀደምን፣
ካስተዋልን፣ በረከቱን እናገኛለን!
(በተጨማሪም መዝ. 97:10ን፣ ማቴ. 22:37ን፣ ዮሐ. 21:15-17ን እና ሥራ 10:42ን ተመልከት።)