መዝሙር 130
ይቅር ባይ ሁኑ
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ በፍቅሩ
ተወዳጅ ልጁን ሰጠን።
ኃጢያታችን እንዲሰረይ፣
ድል እንዲነሳ ሞትን።
ከልብ ንስሐ ከገባን፣
ይቅርታ ’ናገኛለን፤
በ’የሱስ ቤዛ በማመን
ምሕረቱን ከለመንን።
2. ምሕረት ’ምናገኘው
አምላክን ስንመስለው ነው፤
በነፃ ይቅር በማለት፣
ለሌላው ስናዝን ነው።
ምሬትና ቂምን ትተን
እንኑር ተቻችለን።
ወንድሞችን ’ናክብራቸው፤
እናሳይ ፍቅራችንን።
3. ተወዳጅ ነው ምሕረት፤
ሁላችን እናዳብረው።
ያርቀናል ከጥላቻ፤
ቂም ከመያዝ በሌላው።
ፍቅሩ ወደር የሌለውን
አምላክን ከመሰልን፣
እንደ ይሖዋ ’ባታችን
ከልብ ይቅር ’ንላለን።