-
አዳምና ሔዋንከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-
‘አዳም ኃጢአት እንዲሠራ የአምላክ ፈቃድና ዕቅድ ነበር’
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ብዙ ሰዎች እንደዚያ ይላሉ። ይሁን እንጂ እርስዎ አንድ ነገር እንዳደርግ ቢነግሩኝና ባደርግ ስለሠራሁት ሥራ ይኮንኑኛል? . . . ታዲያ አዳም ኃጢአት የሠራው በአምላክ ፈቃድ ከነበረ ለምን እንደ ኃጢአተኛ ተቆጥሮ ከኤደን ተባረረ? (ዘፍ. 3:17–19, 23, 24)’
ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘ጥሩ ጥያቄ ነው። ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ እግዚአብሔር ምን ዓይነት አምላክ መሆኑን የሚመለከት ነው። አንድ ሰው እኛ ራሳችን ባወጣነው ዕቅድ መሠረት ቢሠራ እርሱን መኮነን ትክክል ወይም ፍቅር ያለበት ይሆናል?’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘ይሖዋ የፍቅር አምላክ ነው። (1 ዮሐ. 4:8) መንገዶቹ ሁሉ ፍትሐዊ ናቸው። (መዝ. 37:28፤ ዘዳ. 32:4 አዓት ) አዳም ኃጢአት እንዲሠራ የአምላክ ፈቃድ አልነበረም። እንዲያውም አምላክ አስጠንቅቆት ነበር። (ዘፍ. 2:17)’ (2) ‘አምላክ ዛሬ ለእኛ ምርጫ እንደሚሰጠን ሁሉ ለአዳምም የፈለገውን እንዲመርጥ ነፃነት ሰጥቶት ነበር። ፍጹም መሆኑ አለመታዘዝን እንዳይመርጥ አያግደውም ነበር። አዳም የአለመታዘዝ ውጤት ሞት እንደሚሆን ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም እንኳ በአምላክ ላይ ማመፅን መረጠ።’ (በተጨማሪ ገጽ 142, 143ን ተመልከት።)
-
-
የቀድሞ አባቶችን ማምለክከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
የቀድሞ አባቶችን ማምለክ
ፍቺ:- የቀድሞ አባቶች በማይታይ ዓለም ውስጥ በሕይወት ይኖራሉ፤ ስለሆነም ሕያዋን የሆኑትን ሰዎች ሊረዷቸው ወይም ሊጐዷቸው ይችላሉ፤ ስለዚህ እነርሱን ለማስደሰት (በአንድ ዓይነት ሥርዓት ወይም በሌላ መንገድ) አክብሮት ወይም አምልኮ መስጠት ይገባል የሚል እምነት ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አይደለም።
የሞቱት የቀድሞ አባቶች በሕይወት ያሉት የሚሠሩትን ሊያውቁና እርዳታ ሊያደርጉላቸው ይችላሉን?
መክ. 9:5:- “ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን አንዳች አያውቁም።”
ኢዮብ 14:10, 21:- “ሰው ግን ይሞትና ይጋደማል፤ እርሱስ ወዴት አለ? ልጆቹ ቢከብሩ አያውቅም።”
-