የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ደም
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
    • ነበር። አሁን ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቀው የሕፃናትና የልጆች የልብ ቀዶ ሕክምና እንኳን ያላንዳች ችግር እየተከናወነ ነው።”—ካርዲዮቫስኩላር ኒውስ፣ የካቲት 1984፣ ገጽ 5

      አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-

      ‘ደም አንወስድም እያላችሁ ልጆቻችሁ እንዲሞቱ ታደርጋላችሁ። ይህ ጭካኔ ይመስለኛል’

      እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘አደጋ የማያደርሱ ሌሎች በደም ሥር የሚሰጡ የሕክምና ዓይነቶችን እንዲወስዱ ግን እንፈቅዳለን። እንደ ኤድስ፣ ሄፓታይተስና ወባ የመሳሰሉትን በሽታዎች የማስተላለፍ አደጋ የሌለባቸውን በደም ሥር የሚሰጡ ሕክምናዎችን እንቀበላለን። ማንኛውም ልጁን የሚወድ ወላጅ እንደሚያደርገው ሁሉ እኛም ልጆቻችን ከሁሉ የተሻለ ሕክምና እንዲያገኙ እንፈልጋለን።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘አንድ ሰው ብዙ ደም ከፈሰሰው አንገብጋቢው ነገር በደም ሥር የሚዘዋወረውን ፈሳሽ መጠን መተካት ነው። እንደሚያውቁት ደማችን ከመቶ 50 እጅ በላይ የሚሆነው ውኃ ሲሆን ቀይና ነጭ የደም ሴሎች እንዲሁም ሌሎች ንጥረ ነገሮች ይገኙበታል። ብዙ ደም በሚፈስበት ወቅት ሰውነት ራሱ ለመጠባበቂያ ያስቀመጣቸውን የደም ሴሎች ወደ ደም ሥር በመጨመር አዲስ ሴሎች በአፋጣኝ እንዲፈጠሩ ያደርጋል። ሆኖም የፈሳሹን መጠን ዝቅ እንዳይል ማድረግ ያስፈልጋል። ለዚህም የደም ተዋጽኦ በማይጨመርበትና የፈሳሹን መጠን ከፍ በሚያደርገው ፕላዝማ ኤክስፓንደር መጠቀም ይቻላል። እኛም ይህን ዓይነት ሕክምና እንቀበላለን።’ (2) ‘የደምን ፈሳሽ መጠን ከፍ የሚያደርጉ ፕላዝማ ኤክስፓንደርስ በሺህ በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ተሞክረው እጅግ በጣም ጥሩ የሆኑ ውጤቶችን አስገኝተዋል።’ (3) ‘ለእኛ ከዚህም የበለጠ በጣም አስፈላጊ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ በ⁠ሥራ 15:28, 29 ላይ የሚናገረው ነው።’

      ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘ሐሳብዎ ይገባኛል። የእርስዎ ልጅ በዚህ ሁኔታ ላይ ቢገኝ ምን እንደሚያደርጉ አስበው የተናገሩ መሰለኝ። ወላጆች እንደመሆናችን የልጆቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን፤ አይደለም እንዴ? ስለዚህ እንደ እርስዎና እንደ እኔ ያሉ ሰዎች ለልጆቻችን አንዳንድ የሕክምና ዓይነቶች እንዲደረጉላቸው አንፈቅድም የምንልበት በቂ የሆነ አስገዳጅ ምክንያት እንደሚኖረን አያጠራጥርም።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘የአምላክ ቃል በሥራ 15:28, 29 ላይ የሚናገረው ቃል የአንዳንድ ወላጆችን አስተሳሰብ የሚነካው አይመስልዎትም?’ (2) ‘እንግዲያው ጥያቄው የአምላክን ትእዛዞች ለማክበር የሚያስችለን በቂ እምነት አለን ወይ? የሚል ነው።’

      ‘ደም በመውሰድ አታምኑም’

      እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ጋዜጦች የይሖዋ ምሥክሮች ደም አንወስድም በማለታቸው ሊሞቱ ነው የሚሉ ዜናዎችን አውጥተዋል። እርስዎም እንዲህ ያሉት ይህን በማስታወስ ይሆን? . . . እንዲህ ያለውን አቋም የያዝነው ለምንድን ነው?’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘ሕይወትዎን አሳልፈው እስከሚሰጧቸው ድረስ ባለቤትዎን ይወዷቸዋል? . . . ሕይወታቸውን ለአገራቸው ሲሉ የሚሠዉ ሰዎችም አሉ፤ ጀግኖች ይባሉ የለም? ነገር ግን በዚህ ምድር ላይ ካለ ከማንኛውም ሰው ወይም ነገር የሚበልጥ አለ፤ እርሱም አምላክ ነው። ለእርሱ ባለዎት ፍቅር ወይም ለአገዛዙ ባለዎት ታማኝነት የተነሣ ሕይወትዎን አይሠዉም?’ (2) ‘በእርግጥ እዚህ ላይ የሚነሣው ጥያቄ ለአምላክ ታማኝ የመሆን ጉዳይ ነው። ከደም እንድንርቅ የሚያዘን የአምላክ ቃል ነው። (ሥራ 15:28, 29)’

      ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘ዛሬ የይሖዋ ምሥክሮች የማያደርጓቸው በሰዎች ግን የተለመዱ እንደ ውሸት፣ ምንዝር፣ ስርቆት፣ ሲጋራ ማጨስና እርስዎ እንደጠቀሱት ደም መውሰድ የመሳሰሉ ብዙ ነገሮች አሉ። ከነዚህ ነገሮች የምንርቀው ለምንድን ነው? ሕይወታችንን የምንመራው በአምላክ ቃል ስለሆነ ነው።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) “ከደም ራቁ’ ብሎ የሚያዘን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ ያውቁ ነበርን? ባሳይዎት ደስ ይለኛል። (ሥራ 15:28, 29)’ (2) ‘አምላክ የመጀመሪያዎቹን ወላጆቻችንን አዳምንና ሔዋንን ከአንዷ ዛፍ ፍሬ በስተቀር በገነት ከሚገኙት ዛፎች ሁሉ እንዲበሉ ነግሯቸው እንደነበረ ሳያስታውሱ አይቀሩም። እነርሱ ግን ሳይታዘዙ ቀርተው ከተከለከለው ፍሬ በመብላታቸው የነበራቸውን ነገር በሙሉ አጡ። እንዴት ያለ ሞኝነት ነበር! እርግጥ ዛሬ ከፍሬው እንዳይበላ የተከለከለ ዛፍ የለም። ይሁን እንጂ ከኖኅ ዘመን የጥፋት ውኃ በኋላ አምላክ የሰው ልጆች እንዳያደርጉ የከለከላቸው አንድ ነገር አለ። እርሱም ደም መውሰድ ነው። (ዘፍ. 9:3, 4)’ (3) ‘ስለዚህ እዚህ ላይ ጥያቄው በአምላክ ላይ እምነት አለን ወይ? የሚል ነው። እርሱን ብንታዘዘው በመንግሥቱ ውስጥ ፍጽምና ያለበት የዘላለም ሕይወት የማግኘት ተስፋ ይኖረናል። ብንሞትም እንኳ ትንሣኤ እንደሚኖረን አረጋግጦልናል።’

      ‘ዶክተር “ደም የማትወስድ ከሆነ ትሞታለህ” ቢልስ ምን ታደርጋላችሁ?’

      እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ሁኔታው የዚያን ያህል አስጊ ከሆነ በሽተኛው ደም ቢሰጠው እንደማይሞትስ ዶክተሩ ዋስትና ሊሰጥ ይችላል?’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- ‘ይሁን እንጂ መልሶ ሕይወት ሊሰጥ የሚችል አለ፣ እርሱም አምላክ ነው። ከሞት ጋር ፊት ለፊት በምንፋጠጥበት ጊዜ የአምላክን ሕግ በመጣስ ለአምላክ ጀርባችንን መስጠት ትክክለኛ ውሳኔ ይመስልዎታል? እኔ በአምላክ ላይ ጠንካራ እምነት አለኝ። እርስዎስ? የአምላክ ቃል በልጁ የሚያምኑ ሁሉ ትንሣኤ እንዳላቸው ተስፋ ይሰጣል። ይህን ያምናሉ? (ዮሐ. 11:25)’

      ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘እሱ ያለ ደም ቀዶ ሕክምና ማድረግ እንዴት እንደሚቻል አያውቅ ይሆናል። ከተቻለ በዚህ ረገድ ልምድ ካለው ዶክተር ጋር እንዲገናኝ ለማድረግ እንሞክራለን ወይም ሌላ ዶክተር እንዲያክመን እናደርጋለን።’

  • እንደገና መወለድ
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
    • እንደገና መወለድ

      ፍቺ:- እንደገና መወለድ በውኃ መጠመቅን (‘ከውኃ መወለድን’) እና በአምላክ መንፈስ ተወልዶ (‘ከመንፈስ በመወለድ’) የአምላክን ልጅነት አግኝቶ በመንግሥቱ የመካፈልን ተስፋ ማግኘትን የሚያጠቃልል ነገር ነው። (ዮሐ. 3:3–5) ኢየሱስና ከእርሱ ጋር ሆነው ሰማያዊውን መንግሥት የሚወርሱት 144,000ዎች ይህን ዓይነት ልደት አግኝተዋል።

      “እንደገና መወለድ” ለአንዳንድ ክርስቲያኖች አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

      አምላክ የተወሰነ ቁጥር ያላቸው የታመኑ ሰዎች በሰማያዊው መንግሥት ከኢየሱስ ጋር እንዲሆኑ ዓላማ አለው

      ሉቃስ 12:32:- “አንተ ታናሽ መንጋ፣ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ።”

      ራእይ 14:1–3:- “አየሁም፣ እነሆም፣ በጉ [ኢየሱስ ክርስቶስ] በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፣ ከእርሱም ጋር . . . [ከምድር የተዋጁት] መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።” (“ሰማይ” በሚለው ርዕስ ገጽ 166, 167⁠ን ተመልከት።)

      ሰዎች ሥጋና ደም ይዘው ወደ ሰማይ ሊሄዱ አይችሉም

      1 ቆሮ. 15:50:- “ወንድሞች ሆይ፣ ይህን እላለሁ:- ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፣ የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ