-
እንደገና መወለድከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
አንድ ሰው እንዲህ ቢልስ:-
‘እንደገና ተወልጃለሁ’
እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘እንዲህ ሲሉ አንድ ቀን በሰማይ ከክርስቶስ ጋር እንደሚሆኑ ተስፋ ያደርጋሉ ማለት ነው፤ አይደለም እንዴ? . . . ነገር ግን ወደ ሰማይ የሚሄዱ ሰዎች ወደዚያ የሚሄዱት ምን ለማድረግ እንደሆነ አስበው ያውቃሉ?’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘ከክርስቶስ ጋር ነገሥታትና ካህናት ሆነው ይገዛሉ። (ራእይ 20:6፤ 5:9, 10) እነዚህ “ታናሽ መንጋ” እንደሚሆኑ ኢየሱስ ተናግሯል። (ሉቃስ 12:32)’ (2) ‘ነገሥታት ከሆኑ ደግሞ የሚገዟቸው ተገዥዎች መኖር አለባቸው። ታዲያ እነዚህ እነማን ናቸው? . . . ሰዎች ሲነግሩኝ በጣም አስገራሚ ሆነው ያገኘኋቸውን አንዳንድ ነጥቦች ብገልጽልዎት ደስ ይለኛል። (መዝ. 37:11, 29፤ ምሳሌ 2:21, 22)’
‘እንደገና ተወልደሃል?’
እንዲህ ብለህ ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ሰዎች ‘እንደገና ስለ መወለድ’ ጉዳይ ሁልጊዜ አንድ ዓይነት ትርጉም እንደማይሰጡ ተረድቻለሁ። እርስዎ “እንደገና መወለድ” ሲሉ ምን ማለትዎ እንደሆነ ሊነግሩኝ ይችላሉ?’
ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘ኢየሱስን እንደ ግል አዳኜ አድርጌ በመቀበል መንፈስ ቅዱስ የተሰጠኝ መሆኑን ለማወቅ ነው የፈለጉት፤ አይደለም? እንደዚህ ከሆነ መልሱ አዎን የሚል መሆኑን ላረጋግጥልዎት እወዳለሁ። ይህ ባይሆን ኖሮ ስለ ኢየሱስ ከእርስዎ ጋር ባልተነጋገርሁ ነበር።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘መንፈስ ቅዱስ ስለመቀበል በማስብበት ጊዜ ክርስቲያን ነን በሚሉት በብዙዎች ዘንድ ያ መንፈስ እንደሌለ የሚያሳይ ማስረጃ አያለሁ። (ገላ. 5:22, 23)’ (2) ‘ሁሉም ሰዎች እነዚህን አምላካዊ ባሕርያት ቢያሳዩ ኖሮ በዚህች ምድር ላይ መኖር አያስደስትዎትም ነበር? (መዝ. 37:10, 11)’
ሌላ አማራጭ:- ‘እንደዚህ ሲሉ “ክርስቶስን እንደ አዳኝህ አድርገህ ተቀብለኸዋል ወይ?” ማለትዎ ከሆነ መልሴ አዎን ነው። ሁሉም የይሖዋ ምሥክሮች ኢየሱስን እንደዚያ አድርገው ይመለከቱታል። ነገር ግን ለእኛ እንደገና መወለድ ሲባል ከዚህ የበለጠ ነገርን ይጨምራል።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘ኢየሱስ እንደገና ስለመወለድ በገለጸበት ጊዜ ወደ አምላክ መንግሥት ለመግባት ይኸውም የአምላክ መንግሥት አባል ወይም የሰማያዊ አስተዳደሩ ክፍል ለመሆን እንደገና መወለድ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግሯል። (ዮሐ. 3:5)’ (2) ‘ከዚህ በተጨማሪ ግን መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉ ብዙ ሰዎች የዚያች መንግሥት ደስተኛ ተገዥዎች ሆነው በዚህች ምድር ላይ እንደሚኖሩ ይገልጻል። (ማቴ. 6:10፤ መዝ. 37:29)’
ተጨማሪ ሐሳብ:- የሰማያዊ ክፍል የሆኑት እንዲህ ብለው ሊመልሱ ይችላሉ:- ‘አዎን እንደገና ተወልጃለሁ፤ ነገር ግን ስለተሰጠን ቦታ ከመጠን ያለፈ እንዳንመካ መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንንም ያስጠነቅቃል። አምላክና ክርስቶስ ከእኛ የሚፈልጉብንን በእርግጥ እያደረግን መሆናችንን ለማረጋገጥ ራሳችንን መመርመር ያስፈልገናል። (1 ቆሮ. 10:12)’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- ‘ኢየሱስ በእውነተኛ ደቀ መዛሙርቱ ላይ ምን ኃላፊነት ጥሎባቸዋል? (ማቴ. 28:19, 20፣ 1 ቆሮ. 9:16)’
-
-
መናዘዝ/ማሳወቅከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
-
-
መናዘዝ/ማሳወቅ
ፍቺ:- አንድ ሰው (1) እምነቱን ወይም (2) የሠራውን ኃጢአት በሕዝብ ፊት ወይም በምሥጢር መናገሩ ወይም ማሳወቁ በእንግሊዝኛ “ኮንፌሽን” ይባላል። ይህም መናዘዝ ወይም ማሳወቅ ተብሎ ሊተረጐም ይችላል።
የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የምታስተምረው (ለአንድ ቄስ በምሥጢር የሚነገር) ምሥጢራዊ ኑዛዜን የሚጨምረው የማስታረቅ ሥርዓት ቅዱስ ጽሑፋዊ ድጋፍ አለውን?
ኑዛዜው ለቄሱ የሚነገርበት ሥርዓት
የተለመደውና እስከ ዛሬ ድረስ የሚሠራበት ሥርዓት:- “አባቴ ይፍቱኝ፣ ኃጢአት ሠርቻለሁ። ኃጢአቴን ከተናዘዝሁ [ይህን ያህል ጊዜ] ሆኖኛል” የሚል ነው።—ዩ ኤስ ካቶሊክ መጽሔት፣ ጥቅምት 1982፣ ገጽ 6
ማቴ. 23:1, 9:- “ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ነገራቸው:- . . . አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም:- አባት ብላችሁ አትጥሩ።”
ይቅር ሊባሉ የሚችሉ ኃጢአቶች
“ማንኛውም ኃጢአት ምንም ያህል ከባድ ቢሆን ይቅር ሊባል እንደሚችል ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜ ስታስተምር ቆይታለች።”—ዘ ካቶሊክ ኢንሳይክሎፔድያ (የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማትቀበለውን እምነትና ጽሑፎችን ለማሳተም የምትሰጠውን ፈቃድ የያዘ)፣ አር ሲ ብሮደሪክ (ናሽቪል፣ ቴነሲ፣ 1976)፣ ገጽ 554
-