የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በዘመናችን መቶ ዓመት ባስቆጠረው ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት እየተካፈላችሁ ነውን?
    የመንግሥት አገልግሎት—2003 | ግንቦት
    • ያስፈልገናል። በእኛ አገር ከቤት ወደ ቤት ስንሄድ በአብዛኛው አንድ ሰው ቤት ውስጥ አናጣም። ብዙውን ጊዜ ሰዎች ለመወያየት ፈቃደኞች ከመሆናቸውም በላይ በቀላሉ ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ እንችላለን። ተመላልሶ መጠየቅ በማድረግም ረገድ ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል።

      3 ከቤት ወደ ቤት ማገልገል በይሖዋ ላይ መመካትን ስለሚጠይቅብንና የአምላክ ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን ለመጠቀም አጋጣሚ ስለሚከፍትልን መንፈሳዊነታችንን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በእርግጥም በዚህ መንገድ ክልሎችን መሸፈናችን መጽሔቶችን ከማበርከት በተጨማሪ በአገልግሎታችን መጽሐፍ ቅዱስን እንድንጠቀም ያስችለናል። ይህ የአገልግሎቱ ዘርፍ የወንድማማች ማኅበራችን መለያ በሆነውና ኢየሱስ ክርስቶስ ባስጀመረው የአገልግሎት ዘዴ መካፈል ስለሚያስችለን ልዩ ደስታ ይሰጠናል።

      4 ከቤት ወደ ቤት ማገልገል የራሱ የሆኑ ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንደሚኖሩት እሙን ነው። ቤታቸው ስለሄድን በጣም የሚያመናጭቁን ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ሆኖም አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች እንዲህ ያለ ምላሽ የሚሰጡት በቀጥታ ለእኛ ሳይሆን ለይሖዋና ለመንግሥቱ እውነቶች መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ይህንን ካስታወስን የሚደርስብንን መከራ እንደ ደስታ ልንቆጥረው እንችላለን። ማቴዎስ 5:​11, 12 እና ፊልጵስዩስ 1:27-29 ይህንን ያጎሉልናል።

      5 አልፎ አልፎ አንዳንድ ሃይማኖታዊ አክራሪዎች ረብሻ እንደፈጠሩ መስማታችን በዚህ የአገልግሎት ዘርፍ ከመካፈል ወደ ኋላ እንድንል ሊያደርገን ይገባልን? ሐዋርያቱ ተመሳሳይ ሁኔታ ሲያጋጥማቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ኢየሱስ በማቴዎስ 10:26-31 ላይ የሰጣቸውን ምክር ማስታወሳችን ትክክለኛ አመለካከት እንድንይዝ ሊረዳን ይችላል። በእርግጥም ይሖዋ እንደሚመራንና እንደሚጠብቀን ልንተማመን እንችላለን። ለምሳሌ ያህል፣ ከወረዳ የበላይ ተመልካቾቻችን አንዱ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ በግምት ከ1, 500 ሰዓታት በላይ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት በማሳለፉ በርካታ አስደሳች ተሞክሮዎችን ያገኘ ሲሆን ረብሻ የሚያስነሱ ሰዎች ያጋጠሙት ሁለት ጊዜ ብቻ ነበር። በእነዚህም ጊዜያት ቢሆን ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰበትም። እንደዚህ ዓይነት ተቃውሞ አክራሪ ከሆኑ ዘመዶቻችን ወይም ወደ ክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ስንሄድ መንገድ ላይ ከሚያጋጥሙን ሰዎች ሊሰነዘርብን እንደሚችል ማስታወሳችን ከቤት ወደ ቤት ለሚደረገው አገልግሎት ትክክለኛ አመለካከት እንድንይዝ ይረዳናል። ሆኖም በእነዚህ ጊዜያት በይሖዋ እንደምንታመን የታወቀ ነው።​—⁠ምሳሌ 29:25

      6 የአገልግሎት ክልላችንን ለመሸፈን ልዩ ዘመቻ በምናደርግበት በዚህ ወቅት ከቤት ወደ ቤት ለሚደረገው አገልግሎት ቅድሚያ መስጠታችን ተገቢ ነው። ይህም አብዛኛውን ጊዜያቸውን በቤታቸው አካባቢ የሚያሳልፉ ሰዎች ውድ የሆነውን መልእክታችንን እንዲሰሙ አጋጣሚ ይከፍትላቸዋል። ይሁን እንጂ ከዚያ በኋላ ባለው ጊዜም ቢሆን ሁላችንም በዚህ የአገልግሎታችን ዘርፍ በድፍረትና በቅንዓት ለመካፈል ጥረት እናድርግ። ይሖዋ እንደሚባርከን ምንም ጥርጥር የለውም። እኛም ሐዋርያው ጳውሎስ በሥራ 20:21, 26 (NW ) ላይ እንደተናገረው ‘የተሟላ ምስክርነት ሰጥቻለሁ’ ስለዚህም ‘ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ ነኝ’ ብለን መናገር በመቻላችን እርካታ እናገኛለን።

  • የየካቲት የአገልግሎት ሪፖርት
    የመንግሥት አገልግሎት—2003 | ግንቦት
    • የየካቲት የአገልግሎት ሪፖርት

      አማ. አማ. አማ. አማ. 

      ብዛት:- ሰዓትመጽሔ.ተ.መ. መ/ቅ.ጥ.

      ልዩ አቅኚ 174126.519.478.86.1  

      አቅኚ 56866.67.726.32.1  

      ረዳት አቅኚ 31154.35.716.21.0  

      አስፋፊ 5,76212.11.84.60.4  

      ጠቅላላ 6,815

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ