-
ትሕትናን ልበሱየመንግሥት አገልግሎት—2003 | መስከረም
-
-
ትሕትናን ልበሱ
1 አንድ ልጅ እግር እረኛ በይሖዋ በመተማመን ኃያል የሆነን ጦረኛ አሸነፈ። (1 ሳሙ. 17:45-47) አንድ ባለጸጋ ሰው የደረሰበትን መከራ በጽናት ተቋቋመ። (ኢዮብ 1:20-22፤ 2:9, 10) የአምላክ ልጅ ትምህርቱን ያገኘው ከአባቱ መሆኑን ተናገረ። (ዮሐ. 7:15-18፤ 8:28) በሦስቱም ሁኔታዎች ላይ ጎልቶ የሚታየው ባሕርይ ትሕትና ነው። ዛሬም በተመሳሳይ የሚያጋጥሙንን የተለያዩ ሁኔታዎች ለመወጣት ትሕትና በጣም ይረዳናል።—ቆላ. 3:12
2 በምንሰብክበት ጊዜ:- ክርስቲያን አገልጋዮች እንደመሆናችን መጠን በዘራቸው፣ በባህላቸው ወይም በአስተዳደጋቸው ምክንያት አድልዎ ሳናደርግ ለሁሉም ዓይነት ሰዎች ምሥራቹን በትሕትና እንሰብካለን። (1 ቆሮ. 9:22, 23) አንዳንዶች ቢያመናጭቁን ወይም ለመንግሥቱ መልእክት ንቀት የተሞላበት ምላሽ ቢሰጡን አጸፋውን ከመመለስ ይልቅ የሚገባቸውን ሰዎች በትዕግሥት መፈለጋችንን እንቀጥላለን። (ማቴ. 10:11, 14) እኛ ከምናቀርበው ከማንኛውም ሐሳብ ይልቅ የአምላክ ቃል ይበልጥ አሳማኝ እንደሆነ በመገንዘብ የሰዎችን ትኩረት ወደ ቃሉ ለማዞር እንጥራለን እንጂ በእውቀታችን ወይም በትምህርታችን ልናስደምማቸው አንሞክርም። (1 ቆሮ. 2:1-5፤ ዕብ. 4:12) የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል ይሖዋ እንዲመሰገን እናደርጋለን።—ማር. 10:17, 18
3 በጉባኤ ውስጥ:- ክርስቲያኖች ‘እርስ በርሳቸው እየተዋረዱ ትሕትናን እንደ ልብስ መታጠቅ’ አለባቸው። (1 ጴጥ. 5:5) ሌሎች ከእኛ እንደሚበልጡ አድርገን የምናስብ ከሆነ ወንድሞቻችን እንዲያገለግሉን ከመጠበቅ ይልቅ እነርሱን ማገልገል የምንችልባቸውን መንገዶች እንፈልጋለን። (ዮሐ. 13:12-17፤ ፊልጵ. 2:3, 4) የመሰብሰቢያ አዳራሹን ማጽዳትን የመሳሰሉ ሥራዎች ክብራችንን እንደሚነኩ አድርገን ማሰብ አይገባንም።
4 ትሕትና ‘እርስ በእርሳችን በፍቅር እንድንታገሥ’ ስለሚያስችለን በጉባኤ ውስጥ ሰላምና አንድነት ለማስፈን ይረዳል። (ኤፌ. 4:1-3) ለጉባኤው አመራር እንዲሰጡ ለተሾሙት ወንድሞች እንድንገዛ ይረዳናል። (ዕብ. 13:17) የሚሰጠንን ማንኛውንም ምክር ወይም ተግሣጽ እንድንቀበል ያነሳሳናል። (መዝ. 141:5) ከዚህም በላይ ትሕትና በጉባኤ ውስጥ የሚሰጠንን ማንኛውንም ኃላፊነት በመወጣት ረገድ በይሖዋ እንድንታመን ያደርገናል። (1 ጴጥ. 4:11)
-
-
“ለአምላክ ክብር ስጡት” የ2003 የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባየመንግሥት አገልግሎት—2003 | መስከረም
-
-
“ለአምላክ ክብር ስጡት” የ2003 የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ
1 ይሖዋ ታማኝ በሆነው በነቢዩ በኢሳይያስ አማካኝነት “ወገኔ ሆይ፣ አድምጠኝ፤ ሕዝቤ ሆይ፣ ስማኝ” የሚል ትእዛዝ አስተላልፏል። (ኢሳ. 51:4) ከጊዜ ወደ ጊዜ በጣም አስጨናቂ እየሆነ በሚሄደው በዚህ የመጨረሻ ቀን ከመቼውም ይበልጥ ለይሖዋ ትእዛዝ ትኩረት መስጠት አስፈላጊ ነው ቢባል አንስማማም? ይሖዋን ‘የምንሰማበት’ አንደኛው መንገድ ለአምልኮ እንድንሰበሰብ የሰጠንን ትእዛዝ በማክበር ነው። በዓመት አንድ ጊዜ በምናደርገው የአውራጃ ስብሰባ ላይ በአንድነት ተሰብስበን ለመማር ያለንን ልዩ አጋጣሚ በጉጉት እንጠባበቃለን!
2 በሦስቱም ቀን ተገኙ:- በታማኝና ልባም ባሪያ አማካኝነት ከሚቀርበው ትምህርት የተሟላ ጥቅም ለማግኘት በስብሰባው ላይ ተገኝተን ሙሉውን ፕሮግራም መከታተል እንድንችል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እናድርግ። (ማቴ. 24:45) በአውራጃ ስብሰባው ላይ ሦስቱንም ቀን መገኘት እንድትችል አሠሪህን ፈቃድ መጠየቅ ያስፈልግህ ይሆን? ነህምያ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ቅጥሮቿን መልሶ ለመገንባት ንጉሥ አርጤክስስን ፈቃድ ከመጠየቁ በፊት ‘ወደ ሰማይ አምላክ ጸልዮአል።’ (ነህ. 2:4) አንተም በሦስቱም ቀናት ስብሰባው ላይ መገኘት እንድትችል አሠሪህን ፈቃድ ለመጠየቅ ድፍረት እንዲሰጥህ ወደ ይሖዋ መጸለይ ይገባሃል። አሠሪህ ፈቃድ ለመስጠት ባይስማማስ? በአውራጃ ስብሰባዎቻችን ላይ የምናገኘው ሥልጠና ሐቀኞች፣ ትጉዎችና እምነት የሚጣልብን ሠራተኞች እንድንሆን እንደሚረዳን ብትነግረው ፈቃድ ሊሰጥህ ይስማማ ይሆናል። ከዚህም በላይ ከቤተሰባችን አባላት መካከል የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ ካሉ የስብሰባ ፕሮግራማችንን በተቻለ መጠን አስቀድመን መንገራችን አሳቢነት ነው።
3 “የዚች ዓለም መልክ አላፊ” በመሆኑ በመንፈሳዊ ንቁ ሆነን ለመኖር የአውራጃ ስብሰባዎቻችን በጣም ያስፈልጉናል። (1 ቆሮ. 7:31) በስብሰባው ላይ ሁሉንም ቀን ለመገኘት ዝግጅት ማድረግ ጥረት የሚጠይቅ ቢሆንም እንደዚህ ማድረጋችን አያስቆጭም። “ለአምላክ ክብር ስጡት” የተባለው የዚህ ዓመት የአውራጃ ስብሰባ ይሖዋ በሰይጣን ዓለም ላይ የሚያመጣውን ጥፋት በምንጠባበቅበት ጊዜ በአቋማችን ጸንተን መቀጠል እንድንችል ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይሖዋ ያዘጋጀልንን ትምህርት ለመከታተል በአውራጃ ስብሰባው ላይ እንዳንገኝ እንቅፋት የሚሆንብንን ማንኛውንም ነገር እናስወግድ።—ኢሳ. 51:4, 5
-