የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋን እንዲያከብሩት ሌሎችን መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎት—2002 | መስከረም
    • ይሖዋን እንዲያከብሩት ሌሎችን መርዳት

      1 “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት” የሚል እጅግ አስፈላጊ መልእክት በምድር ዙሪያ ላሉ ሰዎች በመታወጅ ላይ ነው። (ራእይ 14:6, 7) ይህን መልእክት በማወጁ ሥራ የመካፈል መብት አግኝተናል። ሰዎች ይሖዋን እንዲፈሩትና እንዲያመልኩት ስለ እርሱ ምን ማወቅ አለባቸው?

      2 ስሙን:- ሰዎች እውነተኛውን አንድ አምላክ ዛሬ ከሚመለኩት በርካታ የሐሰት አማልክት በስም ለይተው ማወቅ ያስፈልጋቸዋል። (ዘዳ. 4:35፤ 1 ቆ⁠ሮ. 8:5, 6) የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች የይሖዋን ገናና ስም ከ7, 000 ጊዜ በላይ ተጠቅመዋል። ለሰዎች በምንመሰክርበት ጊዜ ስለ አምላክ ስም መቼ ብንነግራቸው እንደሚሻል ማሰባችን ተገቢ ነው። ይህ ማለት ግን ስሙን እንደብቃቸዋለን ወይም ለመጥራት እናፍራለን ማለት አይደለም። አምላክ መላው የሰው ዘር ስሙን እንዲያውቅ ይፈልጋል።​—⁠መዝ. 83:18 NW

      3 ባሕርያቱን:- ሰዎች አምላክን ማክበር እንዲችሉ ምን ዓይነት አምላክ እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋቸዋል። ልዩ ስለሆነው ፍቅሩ፣ አቻ ስለሌለው ጥበቡ፣ ስለማይጓደለው ፍትሑ፣ ሁሉን ቻይ ስለሆነው ኃይሉ እንዲሁም ስለ ምሕረቱ፣ ስለ ፍቅራዊ ደግነቱና ስለ ሌሎች ግሩም ባሕርያቱ ልንነግራቸው ይገባል። (ዘጸ. 34:6, 7) በተጨማሪም ሕይወታቸው የተመካው የይሖዋን ሞገስ በማግኘታቸው ላይ እንደሆነ ተገንዝበው ለአምላክ ጤናማ ፍርሃት ማሳደርንና እርሱን ማክበርን መማር አለባቸው።​—⁠መዝ. 89:7

      4 ወደ አምላክ መቅረብ:- ከሚመጣው የአምላክ ፍርድ በሕይወት ለመትረፍ ሰዎች የይሖዋን ስም በእምነት መጥራት አለባቸው። (ሮሜ 10:13, 14፤ 2 ተ⁠ሰ. 1:8) ይህ ደግሞ ስሙንና ባሕርያቱን በማወቅ ብቻ ከመወሰን የበለጠ ነገር ማድረግን ይጠይቃል። ሰዎች በሙሉ ልባቸው በእርሱ በመታመን ከይሖዋ ጋር የግል ዝምድና እንዲመሠርቱ ልንረዳቸው ይገባል። (ምሳሌ 3:5, 6) የተማሩትን በሥራ ላይ ሲያውሉ፣ ወደ አምላክ ልባዊ ጸሎት ሲያቀርቡና እርሱ የሚያደርግላቸውን እርዳታ በሕይወታቸው ውስጥ ሲመለከቱ እምነታቸው የሚጠናከር ሲሆን ይህም ወደ ይሖዋ ይበልጥ እንዲቀርቡ ይረዳቸዋል።​—⁠መዝ. 34:8

      5 የአምላክን ስም በቅንዓት የምናውጅና ሰዎች በእርሱ እንዲታመኑና እንዲፈሩት የምንረዳቸው እንሁን። ሌሎች በርካታ ሰዎች ይሖዋን እንዲያውቁትና ‘የመዳናቸው አምላክ’ አድርገው እንዲያከብሩት መርዳት እንችል ይሆናል።​—⁠መዝ. 25:5

  • ለጽሑፎቻችን አድናቆት ይኑራችሁ
    የመንግሥት አገልግሎት—2002 | መስከረም
    • ለጽሑፎቻችን አድናቆት ይኑራችሁ

      1 ንጉሥ ኢዮስያስ ቤተ መቅደሱን ለመጠገን የሚያስችል ዝግጅት እያደረገ በነበረበት ወቅት ሥራውን እንዲያከናውኑ የተሾሙትን ሰዎች “ታማኞች ስለሆኑም የተሰጣቸውን ገንዘብ መቆጣጠር አያስፈልግም” በማለት ስለ እነርሱ መልካም ቃል ተናግሮ ነበር። (2 ነ⁠ገ. 22:3-7 አ.መ.ት ) እነዚህ ሰዎች በአደራ የተሰጣቸውን ንብረት የያዙበት መንገድ ቅዱስ ለሆኑ ነገሮች አድናቆት እንደነበራቸው ያሳያል። ዛሬም በተመሳሳይ የአምላክን ምሥራች በማወጁ ቅዱስ ሥራ ስንካፈል በእጃችን የተሰጡንን ንብረቶች በታማኝነት መያዝ ይኖርብናል።

      2 በመስክ አገልግሎት:- ጽሑፎቻችን ለያዙት ጠቃሚ መልእክት ያለን አድናቆትና እነርሱን ለማዘጋጀት ስለሚወጣው ወጪ ያለን ግንዛቤ እንደ ውድ አድርገን እንድንይዛቸው ያነሳሳናል። ለመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ልባዊ አድናቆት ለሌላቸው ሰዎች ጽሑፎቻችንን እንዲሁ ማደል አይኖርብንም። አንድ ሰው ለምሥራቹ እምብዛም አድናቆት ካላሳየ በጽሑፎች ፋንታ ትራክት ልንሰጠው እንችላለን።

      3 ጽሑፎችን የምናበረክተው ለያዙት መልእክት አክብሮት እንዳለን በሚያሳይ መንገድ መሆን አለበት። ጽሑፎች ጥቅም ላይ ሳይውሉ እንዳይባክኑ ለማድረግ ተጨማሪ ጽሑፍ ከመውሰዳችሁ በፊት እቤታችሁ ምን ያህል እንዳላችሁ አረጋግጡ። ከእያንዳንዱ እትም ትርፍ መጽሔት በእጃችሁ የሚቀር ከሆነ ከጉባኤው የምትወስዱትን የመጽሔት ብዛት ብትቀንሱ ጥሩ ይሆናል።

      4 ለግል የምንጠቀምባቸው ጽሑፎች:- ማዘዝ የሚገባን በእርግጥ የሚያስፈልጉንን ጽሑፎች ብቻ ነው። በተለይ ዴሉክስ መጽሐፍ ቅዱሶች፣ ባለማጣቀሻ መጽሐፍ ቅዱስ እና እንደ ኮንኮርዳንስ፣ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ፣ ጠለቅ ብሎ ማስተዋል እና አዋጅ ነጋሪዎች ያሉትን በከፍተኛ ወጪ የሚዘጋጁ ትላልቅ ጽሑፎች በምናዝበት ጊዜ ምክንያታዊ መሆን ይገባናል።

      5 በግል ቅጂዎቻችሁ ላይ ስማችሁንና አድራሻችሁን የመጻፍ ልማድ አላችሁ? እንዲህ ማድረጋችሁ የጠፉባችሁን ጽሑፎች ወዲያውኑ ከመተካታችሁ በፊት ፈልጋችሁ እንድታገኙ ይረዳችኋል። የመዝሙር መጽሐፋችሁ፣ መጽሐፍ ቅዱሳችሁ ወይም በጉባኤ የሚጠና ጽሑፍ ከጠፋባችሁ ምናልባት በጉባኤ ወይም በወረዳ ወይም በልዩ ስብሰባ ላይ ጠፍተው የተገኙ እቃዎች በሚቀመጡበት ሥፍራ ልታገኙት ትችላላችሁ።​—⁠ሉቃስ 15:8, 9

      6 በጽሑፎቻችን አጠቃቀም ረገድ ጠንቃቃ ለመሆን ጥረት እናድርግ። ይህ ከይሖዋ በአደራ የተቀበልናቸውን የመንግሥቱን ንብረቶች በታማኝነት እንደምንይዝ የም​ናሳይበት መንገድ ነው።​—⁠ሉቃስ 16:10

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ