መዝሙር 12
የዘላለም ሕይወት ተስፋ ተሰጥቶናል
በወረቀት የሚታተመው
1. የዘላለም ሕይወት ተስፋ
ለሰው ልጆች ተሰጥቷል።
‘ገሮች ምድርን ይወርሳሉ’፤
ተስፋው ይፈጸማል።
(አዝማች)
የዘላለም ሕይወት፣
እንጣር ለማግኘት።
ተስፋው ይታመናል፤
አምላክ ቃል ገብቷል።
2. ምድር ገነት ትሆናለች፤
ሰውም ፍጹም ይሆናል።
ይሖዋ በምድራችን ላይ
ሰላምን ያሰፍናል።
(አዝማች)
የዘላለም ሕይወት፣
እንጣር ለማግኘት።
ተስፋው ይታመናል፤
አምላክ ቃል ገብቷል።
3. በቅርብ ሙታን ይነሳሉ፤
ያኔ ሐዘን ይረሳል።
ይሖዋ በርኅራኄው
እንባን ካይን ያብሳል።
(አዝማች)
የዘላለም ሕይወት፣
እንጣር ለማግኘት።
ተስፋው ይታመናል፤
አምላክ ቃል ገብቷል።