መዝሙር 29
በንጹሕ አቋም መመላለስ
በወረቀት የሚታተመው
(መዝሙር 26)
1. አምላኬ ሆይ፣ ’ባክህ ፍረድልኝ፤ ባንተ ታምኛለሁ፤
ንጹሕ አቋም አለኝ።
ልቤን ከፍተህ ውስጤን ተመልከተኝ፤
መጥፎ ነገር ቢገኝ እባክህ አጥራልኝ።
(አዝማች)
በኔ በኩል ፍጹም ቆርጫለሁ፤
በንጹሕ አቋሜ እመላለሳለሁ።
2. ካታላይ ጋር በጭራሽ አልውልም።
ካስመሳዮችም ጋር አልተባበርም።
ካመፀኞች ጋር አታጥፋ ነፍሴን፤
ከግፈኞችም ጋር አታድርግ እጣዬን።
(አዝማች)
በኔ በኩል ፍጹም ቆርጫለሁ፤
በንጹሕ አቋሜ እመላለሳለሁ።
3. ወድጃለሁ ያምልኮ ቤትህን።
የሙጥኝ ብያለሁ ንጹሕ አምልኮህን።
መሠዊያህን በደስታ ’ዞራለሁ፤
ምስጋናህን ሁሌ ለሰው አሰማለሁ።
(አዝማች)
በኔ በኩል ፍጹም ቆርጫለሁ፤
በንጹሕ አቋሜ እመላለሳለሁ።
(በተጨማሪም መዝ. 25:2ን ተመልከት።)