መዝሙር 52
ልብህን ጠብቅ
በወረቀት የሚታተመው
(ምሳሌ 4:23)
1. ሁልጊዜ ልብህን ጠብቅ፤
ከኃጢያት መንገድ ራቅ።
አምላክ የተሰወረውን፣
ያያል የልብህን።
አንዳንዴ ልብ ያታልላል፤
ከመንገድ ያርቃል።
ሁሌም ለልብህ ተጠንቀቅ፤
ያምላክን ሕግ ጠብቅ።
2. ጸልይ፤ አዘጋጅ ልብህን፤
ለማወቅ አምላክን።
ምስጋናህን፣ ውዳሴህን፣
ግለጽ የውስጥህን።
ይሖዋ የሚነግረንን፣
መታዘዝ አለብን።
ተጣጣር ታማኝ ለመሆን፤
ለማስደሰት ልቡን።
3. ልብህን ጠብቅ፣ መግበው፤
ንጹሕ የሆነውን።
ያምላክ ቃል ልብህን ይንካው፤
ውስጥህን ያድሰው።
አምላክ ይወዳል ሕዝቦቹን፤
በዚህ እምነት አለን።
በሙሉ ልብህ አምልከው፤
ወዳጅህ አድርገው።