መዝሙር 2
ይሖዋ እናመሰግንሃለን
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ እናመሰግንሃለን፣
የእውነት ብርሃን ስለበራልን።
አመስጋኞች ነን ለጸሎት መብታችን፤
እ’ነግርሃለን የውስጣችንን።
2. ለውዱ ልጅህ ይድረስህ ምስጋና፣
በ’ምነት ዓለምን ድል አ’ርጓልና።
ለምትሰጠን አመራር ተመስገን፤
እንደ ቃላችን እንኖራለን።
3. አምላክ ሆይ እናመሰግንሃለን፣
ስለ ክቡር የስብከት ሥራችን።
በቅርቡ ያልፋል መከራ አይኖርም፤
ምስጋና ይድረስህ ለዘላለም።
(በተጨማሪም መዝ. 50:14፤ 95:2፤ 147:7ን እና ቆላ. 3:15ን ተመልከት።)