መዝሙር 36
“አምላክ ያጣመረውን”
በወረቀት የሚታተመው
1. በደስታ፣ በክብር
ተገመደ በሦስት።
ባምላክና በሰው ፊት፣
ቃል ኪዳን ገባላት።
በአምላክ ፊት ማለላት፤
ከልቡ ሊወዳት።
(አዝማች)
‘አምላክ ያጣመረውን፣
ማንም አይለያየው።’
2. መርምረዋል ቃሉን፤
ለማድረግ ፈቃዱን።
እርዳታውን ይሻሉ፤
ታማኞች ለመሆን።
በአምላክ ፊት ቃል ገባች፤
ከልቧ ልትወደው።
(አዝማች)
‘አምላክ ያጣመረውን፣
ማንም አይለያየው።’
(በተጨማሪም ዘፍ. 2:24ን፣ መክ. 4:12ን እና ኤፌ. 5:22-33ን ተመልከት።)