መዝሙር 51
ይሖዋን አጥብቀን እንያዝ
በወረቀት የሚታተመው
(ኢያሱ 23:8)
1. ልዑሉ ይሖዋ ውዳሴ ይገባዋል።
ሥራው ሁሉ ፍጹም ፍትሕን አያጓድል።
የተናገረው ቃል መሬት ጠብ የማይል፤
ይሖዋን እንያዝ፣ እሱ ይበጀናል።
ሥርዓቱን መከተል ምንጊዜም ያዋጣል።
2. ፍትሕና እውነት የዙፋኑ መሠረት፤
ማደሪያው ተላብሷል ታላቅ ግርማና ውበት።
ገሮች ቃሉን ሰምተው ወደሱ ጎርፈዋል፤
ልዑሉን ይሖዋን የሙጥኝ ብለዋል።
አምልኮ፣ ክብር፣ ምስጋና ይገባዋል።
3. ሰማየ ሰማያት ይይዙት ዘንድ አይችሉም።
እሱን ሊቋቋመው የሚችል ጠላት የለም።
ተስፋው ይፈጸማል፤ ይህን እናምናለን።
ይሖዋን የሙጥኝ ብለን እንይዛለን፤
ፈቃዱን ለማድረግ ከልብ እንተጋለን።
(በተጨማሪም ዘዳ. 4:4፤ 30:20ን፣ 2 ነገ. 18:6ን እና መዝ. 89:14ን ተመልከት።)