የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 11/1 ገጽ 3
  • አምላክን መጠየቅ ተገቢ ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክን መጠየቅ ተገቢ ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ክፉዎች የቀራቸው ጊዜ ምን ያህል ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • በይሖዋ በመታመን በሕይወት ኑሩ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • አዳኛችን በሆነው አምላክ ደስ ይበላችሁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • አምላክን በተመለከተ ትክክለኛው ትምህርት የቱ ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 11/1 ገጽ 3

አምላክን መጠየቅ ተገቢ ነው?

አንዳንዶች አምላክን መጠየቅ ስህተት እንደሆነ ይናገራሉ። አምላክ አንዳንድ ነገሮችን የሚፈቅደው ወይም የማይፈቅደው ለምን እንደሆነ መጠየቅ አክብሮት የጎደለው ድርጊት እንደሆነ ይሰማቸው ይሆናል። አንተም እንደዚህ ይሰማሃል?

ከሆነ ብዙ ጥሩ ሰዎች ለአምላክ ጥያቄ አቅርበውለት እንደነበር ስታውቅ ትገረም ይሆናል። አንዳንዶች ለአምላክ ካቀረቧቸው ጥያቄዎች መካከል ከታች ያሉትን እንደ ምሳሌ መመልከት እንችላለን፦

ታማኙ ኢዮብ፦ “ኀጢአተኞች ለምን በሕይወት ይኖራሉ? ለምን ለእርጅና ይበቃሉ? ለምንስ እያየሉ ይሄዳሉ?”—ኢዮብ 21:7

ታማኙ ነቢይ ዕንባቆም፦ “አታላዮችን ለምን ትታገሣለህ? ክፉው ከራሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠውስ፣ ለምን ዝም ትላለህ?”—ዕንባቆም 1:13

ኢየሱስ ክርስቶስ፦ “አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ?”—ማቴዎስ 27:46

በእነዚህ ጥቅሶች ዙሪያ ያለውን ሐሳብ ብትመለከት ይሖዋa አምላክ፣ እነዚህ ሰዎች በቅን ልቦና ተነሳስተው ባቀረቧቸው ጥያቄዎች ቅር እንደተሰኘ የሚያመለክት ነገር አታገኝም። ለነገሩ ይሖዋ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ለማዳመጥ ፈቃደኛ እንደሆነ መገለጹ የሚያስገርም አይደለም። ለምሳሌ ያህል፣ አምላክ ለአካላዊ ጤንነታችን አስፈላጊ የሆኑትን መሠረታዊ ነገሮች እንዲያሟላልን ስንጠይቀው ቅር አይሰኝም። እንዲያውም ልመናዎቻችንን በመስማት ፍላጎታችንን በደስታ ያሟላልናል። (ማቴዎስ 6:11, 33) በተመሳሳይም የሚያስፈልገንን መረጃ በመስጠት አእምሯችንንና ልባችንን ያሳርፍልናል። (ፊልጵስዩስ 4:6, 7) ኢየሱስም ቢሆን ደቀ መዛሙርቱን “ደጋግማችሁ ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ሳታቋርጡ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ” ብሏቸዋል። (ማቴዎስ 7:7) በዚህ ጥቅስ ዙሪያ ያለው ሐሳብ እንደሚያመለክተው ኢየሱስ እየተናገረ የነበረው ቁሳዊ ነገሮችን ስለመቀበል ብቻ ሳይሆን ለምንጠይቃቸው አስፈላጊ ጥያቄዎች መልስ ስለማግኘትም ጭምር ነው።

አምላክን የመጠየቅ አጋጣሚ ብታገኝ ቀጥሎ ካሉት ጥያቄዎች መካከል የትኛውን መጠየቅ ትፈልጋለህ?

  • ሕይወቴ ዓላማ አለው?

  • ስሞት ምን እሆናለሁ?

  • መከራ እንዲደርስብኝ የምትፈቅደው ለምንድን ነው?

“ቅዱስ መጽሐፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፈ” ስለሆነ ለእነዚህ ጥያቄዎች አምላክ የሚሰጠውን መልስ በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማግኘት ትችላለህ። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) አንዳንድ ሰዎች ከላይ የቀረቡትን ጥያቄዎች እንዲጠይቁ ያነሳሳቸውን ምክንያትና መጽሐፍ ቅዱስ ለጥያቄዎቹ የሚሰጣቸውን መልሶች በቀጣዮቹ ርዕሶች ላይ እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።

a የአምላክ ስም ይሖዋ እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተገልጿል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ