መዝሙር 1
የይሖዋ ባሕርያት
በወረቀት የሚታተመው
(ራእይ 4:11)
1. ይሖዋ ሆይ፣ ኃይልህ ታላቅ ነው፤
ሕይወት፣ ብርሃን ካንተ ነው ’ሚገኘው።
ይናገራል ፍጥረት ስለ ኃይልህ፤
ይልቁንም ታላቅ ቀንህ።
2. የዙፋንህ መሠረት ፍትሕ፤
እንከን የለው፣ ጽድቅ ነው ት’ዛዝህ።
ስናጠና ቃልህን በትኩረት፣
ታየን የጥበብህ ጥልቀት።
3. ፍቅርህ ፍጹም፣ አቻ የሌለው፤
አይከፈል፣ ውለታህ ብዙ ነው።
ባሕሪህን፣ ክቡር ስምህንም
እናሳውቅ ለዘላለም።