መዝሙር 37
ቅዱሳን መጻሕፍት በመንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው
በወረቀት የሚታተመው
1. ያምላክ ቃል ነው ብርሃናችን፤
መብራት ለመንገዳችን።
ዘወትር ብንከተለው፣
ነፃ ያወጣል እውነት ነው።
2. በአምላክ መንፈስ ተጽፏል፤
ሕጉን ያስተምረናል።
ሁሉንም ነገር ያቀናል፤
ተግሣጽ፣ ምክር ይሰጠናል።
3. አምላክ በሰጠን በዚህ ቃል፣
የሱን ፍቅር አውቀናል።
በየዕለቱ በማንበብ፣
’ናግኝ ሕይወት እና ጥበብ።
(በተጨማሪም መዝ. 119:105ን እና ምሳሌ 4:13ን ተመልከት።)