መዝሙር 23
ይሖዋ ኃይላችን
በወረቀት የሚታተመው
1. ደጉ ይሖዋ ብርታት፣ ኃይላችን፤
ባንተ ደስ ይለናል አዳኛችን።
ሰዎች ቢሰሙንም ባይሰሙንም፣
መመሥከራችንን አናቆምም።
(አዝማች)
ይሖዋ ’ምባችን፤ ብርታት፣ ኃይላችን፤
ስምህን እናስታውቅ ሌትና ቀን።
ሁሉን ቻይ ይሖዋ ተገናችን፣
መሸሸጊያችን ነህ፤ መከታችን።
2. ደስ ብሎናል፣ እውነትን አወቅን፤
ብርሃን አየን፣ ማስተዋል ኣገኘን።
ት’ዛዝህን ከቃልህ አውቀናል፤
ለመንግሥትህ ለመቆም መርጠናል።
(አዝማች)
ይሖዋ ’ምባችን፤ ብርታት፣ ኃይላችን፤
ስምህን እናስታውቅ ሌትና ቀን።
ሁሉን ቻይ ይሖዋ ተገናችን፣
መሸሸጊያችን ነህ፤ መከታችን።
3. እንታዘዝሃለን በደስታ፤
አንተ ብቻ ነህ የኛ አለኝታ።
ሊያጠቃን ቢነሳብንም ሰይጣን፣
እስከ ሞት ታማኝ እንድንሆን እርዳን።
(አዝማች)
ይሖዋ ’ምባችን፤ ብርታት፣ ኃይላችን፤
ስምህን እናስታውቅ ሌትና ቀን።
ሁሉን ቻይ ይሖዋ ተገናችን፣
መሸሸጊያችን ነህ፤ መከታችን።
(በተጨማሪም 2 ሳሙ. 22:3ን፣ መዝ. 18:2ን እና ኢሳ. 43:12ን ተመልከት።)