የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb16 መጋቢት ገጽ 7
  • ትንሣኤ—በቤዛው አማካኝነት የተገኘ ስጦታ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትንሣኤ—በቤዛው አማካኝነት የተገኘ ስጦታ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በሞት የተለዩህ የምትወዳቸው ሰዎች ያላቸው እውነተኛ ተስፋ
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • ብናዝንም ተስፋ የሌለን አይደለንም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ብቸኛው መፍትሔ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • በሞት የተለዩህ የምትወዳቸው ሰዎች ዳግመኛ በሕይወት ይኖራሉ!
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
mwb16 መጋቢት ገጽ 7

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ትንሣኤ—በቤዛው አማካኝነት የተገኘ ስጦታ

አንዲት ልጅ ከሞተችበት አልጋ ዙሪያ ቤተሰቦቿና ጓደኞቿ ሲያለቅሱ፣ እህቷ ወደፊት ባለው የትንሣኤ ተስፋ ላይ ስታሰላስል

የመታሰቢያው በዓል፣ በቤዛው አማካኝነት ወደፊት በምናገኛቸው በረከቶች ለምሳሌ እንደ ትንሣኤ ባሉ ተስፋዎች ላይ ለማሰላሰል ጥሩ አጋጣሚ ይከፍትልናል። ይሖዋ የሰው ልጆች እንዲሞቱ ዓላማው አልነበረም። የምንወደውን ሰው በሞት ማጣት በሕይወታችን ውስጥ ከሚያጋጥሙን በጣም አሳዛኝ ነገሮች መካከል አንዱ የሆነው ለዚህ ነው። (1ቆሮ 15:26) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ በአልዓዛር ሞት ምክንያት ሲያለቅሱ መመልከቱ አሳዝኖታል። (ዮሐ 11:33-35) ኢየሱስ የአባቱ ፍጹም ነጸብራቅ በመሆኑ ይሖዋ የምንወደውን ሰው በሞት በማጣት የሚደርስብንን ሐዘን ሲመለከት እንደሚያዝን እርግጠኞች መሆን እንችላለን። (ዮሐ 14:7) ይሖዋ አገልጋዮቹን ከሞት የሚያስነሳበትን ጊዜ በጉጉት ይጠባበቃል፤ እኛም ይህን ጊዜ በጉጉት መጠባበቅ ይኖርብናል።—ኢዮብ 14:14, 15

ይሖዋ የሥርዓት አምላክ ስለሆነ ትንሣኤ የሚከናወነው በየተራ እንደሆነ መጠበቁ ምክንያታዊ ነው። (1ቆሮ 14:33, 40) በቀብር ሥርዓት ፈንታ ከሞት የተነሱ ሰዎችን የምንቀበልበት ዝግጅት ይኖራል። በተለይ ሐዘን ሲያጋጥምህ በትንሣኤ ተስፋ ላይ ታሰላስላለህ? (2ቆሮ 4:17, 18) ይሖዋ ቤዛ ስላዘጋጀና የሞቱ ሰዎች ተነስተው በሕይወት እንደሚኖሩ የሚገልጽ ተስፋ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲሰፍር በማድረጉ ታመሰግነዋለህ?—ቆላ 3:15

  • ከሞት ተነስተው ለማየት የምትጓጓው የትኞቹን ጓደኞችህን ወይም ዘመዶችህን ነው?

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከተጠቀሱት ሰዎች መካከል በተለይ እነማንን ለማግኘት ትጓጓለህ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ