የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w08 3/1 ገጽ 3
  • የሰው ዘር መዳን ያስፈልገዋል!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሰው ዘር መዳን ያስፈልገዋል!
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የኢየሱስ ሞት ሊያድንህ የሚችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • መዳን የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ስለ ሞት የሚነገሩ አንዳንድ አፈ ታሪኮችን ጠለቅ ብሎ መመርመር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • የሰው ልጅ ረጅም ዕድሜ ለመኖር የሚያደርገው ጥረት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
w08 3/1 ገጽ 3

የሰው ዘር መዳን ያስፈልገዋል!

በፒትስበርግ፣ ፔንስልቬንያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ አቅራቢያ የሚገኝ አንድ የድንጋይ ከሰል ማዕድን ማውጫ ድንገት በውኃ ተጥለቀለቀ። በዚህም ምክንያት ዘጠኝ ማዕድን ቆፋሪዎች 73 ሜትር ጥልቀት ባለው ጉድጓድ ውስጥ እንደተቀበሩ መውጣት ሳይችሉ ቀሩ። ከሦስት ቀን በኋላ ግን ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጉድጓዱ ወጡ። በሕይወት መትረፍ የቻሉት እንዴት ነው?

የሕይወት አድን ሠራተኞች በማዕድን ማውጫው ካርታና ግሎባል ፖዚሽኒግ ሲስተም በተባለ አቅጣጫ ጠቋሚ መሣሪያ በመታገዝ ሰዎቹ ያሉበትን ቦታ ማወቅ ቻሉ። ከዚያም 65 ሴንቲ ሜትር ስፋት ያለው ጉድጓድ ከቆፈሩ በኋላ በሽቦ የተሠራ በርሜል ሰዎቹ ያሉበት ድረስ በማስገባት አንድ በአንድ አወጧቸው። ሰዎቹም እጅግ የተደሰቱና እፎይታ የተሰማቸው ከመሆኑም ሌላ ሕይወታቸውን የታደጉላቸውን ሠራተኞች አመስግነዋል።

አብዛኞቻችን ዘጠኙ ማዕድን ቆፋሪዎች የነበሩበት ዓይነት ሁኔታ ላያጋጥመን አሊያም ሕይወታችንን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር ላይደርስብን ይችል ይሆናል። ይሁን እንጂ ሁላችንም ከበሽታ፣ ከእርጅና እና ከሞት ማምለጥ ስለማንችል፣ ከእነዚህ ነገሮች የሚታደገን ያስፈልገናል። ታማኝ የእምነት አባት የሆነው ኢዮብ “ከሴት የተወለደ ሰው፣ ዘመኑ አጭርና በመከራ የተሞላ ነው፤ እንደ አበባ ይፈካል፤ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላ ይፈጥናል፤ አይጸናምም” ብሏል። (ኢዮብ 14:1, 2) እነዚህ ቃላት ከ3,500 ዓመታት በፊት የተነገሩ ቢሆኑም ዛሬም እውነት መሆናቸው በግልጽ ይታያል። ምክንያቱም ማንኛችንም ብንሆን አስከፊ ከሆነው ከሞት ማምለጥ አንችልም። የምንኖረው የትም ይሁን የት አሊያም ጤንነታችንን ለመጠበቅ የቱንም ያህል ጥረት እናድርግ ከመከራ፣ ከእርጅና እና ከሞት ባርነት ነፃ የሚያወጣን ያስፈልገናል።

የሳይንስ ሊቃውንትና ሌሎች፣ የሰዎችን የዕድሜ ጣሪያ ለማስረዘም ብርቱ ጥረት ያደርጋሉ። አንድ ድርጅት ዓላማው “አይቀሬ የሆነውን ሞት ድል ማድረግ” እና “የድርጅቱ አባላት የሰው ልጅ ያለመሞት ባሕርይ እንዲኖረው ለማስቻል የሚያደርጉት ጥረት ስኬታማ እንዲሆን መርዳት” መሆኑን ገልጿል። እስካሁን ድረስ ግን ዘመናዊው ሳይንስም ሆነ የሰው ልጆች ያላቸው ከፍተኛ ፍላጎት የሰውን ዕድሜ፣ ሙሴ ከ3,500 ዓመታት በፊት ከተናገረው ከ70 ወይም ከ80 ዓመት ብዙም ፈቅ እንዲል አላደረገውም።—መዝሙር 90:10

ኢዮብ ስለ ሕይወትና ስለ ሞት በነበረው አመለካከት ተስማማህም አልተስማማህ ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ አንተም ከወዳጆችህና ከቤተሰብህ ተለይተህ እንዲሁም ቤትህንና የሠራሃቸውን ነገሮች ሁሉ ትተህ ‘እንደ ጥላ ፈጥነህ’ ማለፍህ ማለትም መሞትህ አይቀርም። የጥንቷ እስራኤል ንጉሥ የነበረው ጠቢቡ ሰሎሞን እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁምና፤ መታሰቢያቸው ይረሳል፤ ምንም ዋጋ የላቸውም።”—መክብብ 9:5

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልጸው ሞት በሰው ዘር ላይ እንደ ጨካኝ ገዥ ‘መንገሡ’ አሳዛኝ እውነታ ነው። አዎን፣ ሞት የሰው ልጆች የመጨረሻው ጠላት ነው፤ በመሆኑም ከሞት የሚያድነን ያስፈልገናል። (ሮሜ 5:14፤ 1 ቆሮንቶስ 15:26) በዓለም ላይ ያሉ ጥሩ ሥልጠና ያገኙና ከሁሉ የተሻለ መሣሪያ ያላቸው የድንገተኛ አደጋ ሠራተኞች እንኳ ለዘለቄታው ከሞት እንድታመልጥ ሊረዱህ አይችሉም። ሆኖም የሰው ልጅ ፈጣሪ የሆነው ይሖዋ አምላክ መዳን የምትችልበትን ዝግጅት አድርጓል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ