የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ ከልብ ለቀረበ ጸሎት የሰጠው መልስ
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | ጥቅምት 15
    • 17. ለተቃዋሚዎች የተከፈተው የትኛው አጋጣሚ በቅርቡ ያበቃል? የትኛውን ጸሎት እናስታውሳለን?

      17 እርግጥ ነው፣ አሁንም ተቃዋሚዎች የይሖዋ ምሥክሮችን ማሳደዳቸው እንዳላቆሙ እናውቃለን። እኛም ለተቃዋሚዎቻችንም ጭምር ምሥራቹን መስበካችንን አናቋርጥም። (ማቴ. 24:14, 21) ሆኖም እነዚህ ተቃዋሚዎች ንስሐ ገብተው መዳን እንዲያገኙ የተከፈተላቸው አጋጣሚ በቅርቡ ያበቃል። ከሰው ልጆች መዳን ይበልጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነገር የይሖዋ ስም መቀደስ ነው። (ሕዝቅኤል 38:23⁠ን [NW] አንብብ።)b አስቀድሞ በተነገረው መሠረት ብሔራት በሙሉ የአምላክን ሕዝቦች ለማጥፋት ሲሰባሰቡ መዝሙራዊው “ለዘላለም ይፈሩ፤ ይታወኩም፤ በውርደትም ይጥፉ” በማለት ያቀረበውን ጸሎት እናስታውሳለን።—መዝ. 83:17

      18, 19. (ሀ) የይሖዋን ሉዓላዊነት በመቃወም የሚቀጥሉ ሁሉ ምን ይጠብቃቸዋል? (ለ) ይሖዋ ሉዓላዊነቱን ለመጨረሻ ጊዜ የሚያረጋግጥበት ወቅት መቅረቡ ለአንተ ምን ትርጉም አለው?

      18 የይሖዋን ሉዓላዊነት ለመቃወም ቆርጠው የተነሱ ሁሉ ኃፍረት ተከናንበው ይጠፋሉ። የአምላክ ቃል፣ ‘ለወንጌል ባለመታዘዛቸው’ የተነሳ በአርማጌዶን እርምጃ የሚወሰድባቸው ሰዎች ‘ለዘላለም እንደሚጠፉ’ ይናገራል። (2 ተሰ. 1:7-9) እነዚህ ሰዎች መጥፋታቸው እንዲሁም ይሖዋን በእውነት የሚያመልኩ ሰዎች ከጥፋቱ መዳናቸው ብቸኛው እውነተኛ አምላክ ይሖዋ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይሆናል። ይህ ታላቅ ድል በአዲሱ ዓለም ውስጥ ለዘላለም ሲታወስ ይኖራል። “ጻድቃንና ኀጥአን ከሙታን [ሲነሡ]” ስለ ይሖዋ ታላቅ ሥራ ይማራሉ። (ሥራ 24:15) እነዚህ ሰዎች፣ ለይሖዋ ሉዓላዊነት መገዛት የጥበብ አካሄድ መሆኑን የሚያሳይ አሳማኝ ማስረጃ በአዲሱ ዓለም ውስጥ ይመለከታሉ። ገሮችም ይሖዋ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ መሆኑን አምነው ለመቀበል ጊዜ አይፈጅባቸውም።

  • “ይህ በእርግጥም እጅግ ቅዱስና ታላቅ የሆነው የአምላክ ስም ነው”
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | ጥቅምት 15
    • “ይህ በእርግጥም እጅግ ቅዱስና ታላቅ የሆነው የአምላክ ስም ነው”

      ይህን ሐሳብ የተናገረው የኪዩሳው ኒኮላስ በመባል የሚታወቅ ሰው ሲሆን እንዲህ ያለው በ1430 ባቀረበው ስብከት ላይ ነበር።a ይህ ሰው ስለተለያዩ ነገሮች የማወቅ ፍላጎት የነበረው ሲሆን ካጠናቸው ትምህርቶች መካከል ግሪክኛን፣ ዕብራይስጥን፣ ፍልስፍናን፣ ሒሳብን እንዲሁም ሥነ መለኮትንና ሥነ ፈለክን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ኒኮላስ የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የምትመራባቸውን ሕጎች በማጥናት በ22 ዓመቱ የዶክትሬት ዲግሪውን ያገኘ ሲሆን በ1448 ካርዲናል ሆኖ ተሹሟል።

      ከ550 ዓመታት ገደማ በፊት የኪዩሳው ኒኮላስ፣ በኩስ ከተማ የአረጋውያን መጦሪያ ተቋም አቋቋመ፤ ኩስ በአሁኑ ጊዜ በርንካስትል ኩስ ተብላ የምትጠራ ሲሆን የምትገኘውም ጀርመን ውስጥ ከቦን ከተማ በስተደቡብ 130 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ነው። በአሁኑ ጊዜ፣ መጦሪያ ተቋሙ በነበረበት ሕንፃ ውስጥ የኪዩሳ ቤተ መጻሕፍት ይገኛል፤ ቤተ መጻሕፍቱም ከ310 በላይ ጥንታዊ ጽሑፎችን ይዟል። ከእነዚህ ጥንታዊ ጽሑፎች አንዱ ኮዴክስ ኩሳኑስ 220 ሲሆን ይህ ጽሑፍ ኒኮላስ በ1430 ያቀረበውን ስብከት ይዟል። የኪዩሳው ኒኮላስ፣ ኢን ፕሪንሲፒዮ ኤራት ቬርበም (በመጀመሪያ ቃል ነበረ) በሚል ርዕስ ባቀረበው በዚህ ስብከት ላይ የይሖዋ ስም በላቲን የሚጠራበትን Iehoua (ኢኦዋ) የሚለውን ቃል ተጠቅሟል።b በዚህ ጥንታዊ ጽሑፍ ገጽ 56 ላይ የአምላክን ስም በተመለከተ እንዲህ የሚል ሐሳብ ሰፍሯል:- “አምላክ ለራሱ ያወጣው ስም ነው። ቴትራግራማተንን ማለትም አራት ፊደላትን የያዘው ስም ነው፤ . . . ይህ በእርግጥም እጅግ ቅዱስና ታላቅ የሆነው የአምላክ ስም ነው።” የኪዩሳው ኒኮላስ የተናገረው ይህ ሐሳብ የአምላክ ስም በጥንቶቹ የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የሚገኝ ከመሆኑ ጋር ይስማማል።—ዘፀአት 6:3 የ1879 ትርጉም

      በ15ኛው መቶ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ የተዘጋጀው ይህ ኮዴክስ፣ ቴትራግራማተንን “ኢኦዋ” ብለው ከተረጎሟቸው በዛሬው ጊዜ ከሚገኙ እጅግ ጥንታዊ ጽሑፎች መካከል አንዱ ነው። ይህ ጽሑፍ፣ የአምላክን ስም “ይሖዋ” ከሚለው ስም ጋር በሚመሳሰሉ መጠሪያዎች መጻፍ ለበርካታ መቶ ዘመናት ሲሠራበት የቆየ በጣም የተለመደ አካሄድ እንደነበር የሚያረጋግጥ ተጨማሪ ማስረጃ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ