መዝሙር 77
ይቅር ባይ ሁኑ
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ በፍቅሩ
አንድያ ልጁን ሰጠን።
ኃጢያታችን እንዲሰረይ፣
ድል እንዲነሳ ሞትን።
ከልብ ንስሐ ከገባን፣
ይቅርታ ’ናገኛለን፤
በ’የሱስ ቤዛ በማመን
ምሕረቱን ከለመንን።
2. ምሕረት ’ምናገኘው
አምላክን ስንመስለው ነው፤
በነፃ ይቅር በማለት፣
ለሌላው ስናዝን ነው።
እርስ በርሳችን ’ንቻቻል፤
ሰውን ማስቀየም ይቅር።
ወንድሞችን ’ናክብራቸው፤
እናሳይ ፍቅራችንን።
3. ተወዳጅ ነው ምሕረት፤
ሁላችን እናዳብረው።
ያርቀናል ከጥላቻ፤
ቂም ከመያዝ በሌላው።
ፍቅሩ ወደር የሌለውን
አምላክን ከመሰልን፣
እንደ ይሖዋ ’ባታችን
ከልብ ይቅር ’ንላለን።