መዝሙር 115
መንገዳችንን የተቃና ማድረግ
በወረቀት የሚታተመው
(ኢያሱ 1:8)
1. በአምላክ ቃል ደስ ይለናል፤
’ናንብበው በየ’ለት።
ድምፅ አውጥተን በለሆሳስ
እናሰላስልበት።
አንደበት፣ እርምጃችንን
ይቆጣጠርልን።
(አዝማች)
አንብብ፣ አሰላስል፣ ታዘዝ፤
በረከት ታጭዳለህ።
ሁሌ ካምላክህ ጋር ተጓዝ፤
ስኬት ታገኛለህ።
2. እስራኤላዊ ነገሥታት
እንዲህ ተባሉ ጥንት፦
‘ንጉሡ ለራሱ
ይጻፍ ያምላክን ሕግጋት።
እንዳይበድል በዘመኑ
ያንብብ በየቀኑ።’
(አዝማች)
አንብብ፣ አሰላስል፣ ታዘዝ፤
በረከት ታጭዳለህ።
ሁሌ ካምላክህ ጋር ተጓዝ፤
ስኬት ታገኛለህ።
3. የአምላክን ቃል ስናነብ
ተስፋ ይሰጠናል።
ልባችን ሰላም ያገኛል።
እምነታችን ያድጋል።
አጥብቀን ከያዝን ቃሉን
ብስለት ይኖረናል።
(አዝማች)
አንብብ፣ አሰላስል፣ ታዘዝ፤
በረከት ታጭዳለህ።
ሁሌ ካምላክህ ጋር ተጓዝ፤
ስኬት ታገኛለህ።
(በተጨማሪም ዘዳ. 17:18ን፣ 1 ነገ. 2:3, 4ን፣ መዝ. 119:1ን እና ኤር. 7:23ን ተመልከት።)