ክርስቲያናዊ ሕይወት
መለኮታዊው ትምህርት ጭፍን ጥላቻን ድል ያደርጋል
ይሖዋ አያዳላም። (ሥራ 10:34, 35) “ከሁሉም ብሔራት፣ ነገዶች፣ ሕዝቦችና ቋንቋዎች የተውጣጡ” ሰዎችን ይቀበላል። (ራእይ 7:9) በመሆኑም በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ፣ ጭፍን ጥላቻም ሆነ አድልዎ ቦታ የላቸውም። (ያዕ 2:1-4) ለመለኮታዊው ትምህርት ምስጋና ይግባውና የባሕርይ ለውጥ ባደረጉ ሰዎች በተሞላ መንፈሳዊ ገነት ውስጥ መኖር ችለናል። (ኢሳ 11:6-9) በልባችን ውስጥ ያለውን ጭፍን ጥላቻ ከሥሩ ነቅለን ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋችን አምላክን መምሰል እንደምንፈልግ ያሳያል። —ኤፌ 5:1, 2
ጆኒና ጊደየን፦ ከጠላትነት ወደ ወንድማማችነት የተባለውን ቪዲዮ ተመልከቱ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ፦
አድልዎንና ጭፍን ጥላቻን በማሸነፍ ረገድ መለኮታዊው ትምህርት ሰዎች ከሚያደርጉት ጥረት የላቀ የሆነው እንዴት ነው?
ከዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበራችን ጋር በተያያዘ በጣም የሚያስደንቅህ ነገር ምንድን ነው?
ክርስቲያናዊ አንድነታችንን መጠበቃችን ይሖዋን የሚያስከብረው እንዴት ነው?