መዝሙር 78
‘የአምላክን ቃል ማስተማር’
በወረቀት የሚታተመው
1. ያምላክን ቃል በማስተማር
’ምናገኘው ደስታ፣
ወደር የለው የሚሰማን
ሰላምና ’ርካታ።
በደግነት በማስተማር
’የሱስን ከመሰልን
ጥናቶቻችን ያድጋሉ፤
ወዳምላክ ይቀርባሉ።
2. ቃሉን መንገር ብቻ ሳይሆን
በተግባር ላይ ማዋል
የሰዎችን ልብ ይነካል፤
ትምህርቱን ያስውባል።
ጥሩ ዝግጅት በማድረግ፣
ቃሉን በመመርመር፤
ሌሎችን ብቻ ሳይሆን
ራሳችንን እናስተምር።
3. አምላካችን አስታጥቆናል፤
ሥልጠና ሰጥቶናል።
እንለምነው እንዲረዳን
ስንጸልይ ይሰማል።
ያምላክን ቃል ከወደድን፣
በፍቅር ካስተማርን
ጥናቶች ያድጋሉ፤
አስተማሪዎች ይሆናሉ።
(በተጨማሪም መዝ. 119:97ን፣ 2 ጢሞ. 4:2ን፣ ቲቶ 2:7ን እና 1 ዮሐ. 5:14ን ተመልከት።)