የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • jy ምዕ. 38 ገጽ 96-ገጽ 97 አን. 7
  • ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ጥያቄ አቀረበ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ጥያቄ አቀረበ
  • ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዮሐንስ እምነት ጎድሎት ነበርን?
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • መጥምቁ ዮሐንስ ማን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ኢየሱስ እየጨመረ ዮሐንስ ግን እየቀነሰ ሄደ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
ለተጨማሪ መረጃ
ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
jy ምዕ. 38 ገጽ 96-ገጽ 97 አን. 7
መጥምቁ ዮሐንስ እስር ቤት ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ

ምዕራፍ 38

ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ጥያቄ አቀረበ

ማቴዎስ 11:2-15 ሉቃስ 7:18-30

  • መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ ስለሚጫወተው ሚና ጠየቀ

  • ኢየሱስ ዮሐንስን አደነቀው

መጥምቁ ዮሐንስ ወህኒ ከወረደ አንድ ዓመት ገደማ ሆኖታል። እዚያም ሆኖ ኢየሱስ ስላከናወናቸው ተአምራት ይሰማል። የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት፣ ኢየሱስ በናይን የአንዲትን መበለት ልጅ ከሞት እንዳስነሳ ሲነግሩት ዮሐንስ ምን ተሰምቶት እንደሚሆን አስበው። ያም ቢሆን ዮሐንስ ይህ ምን ትርጉም እንዳለው በቀጥታ ከኢየሱስ መስማት ፈለገ። ስለዚህ ዮሐንስ ሁለት ደቀ መዛሙርቱን ጠራቸው። ምን እንዲያደርጉ ፈልጎ ይሆን? “ይመጣል የተባልከው አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ብለው ኢየሱስን እንዲጠይቁት ላካቸው።—ሉቃስ 7:19

ዮሐንስ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ማቅረቡ ይገርማል? ይህ ታማኝ ሰው ከሁለት ዓመት ገደማ በፊት ኢየሱስን ባጠመቀበት ጊዜ የአምላክ መንፈስ በኢየሱስ ላይ ሲወርድ የተመለከተ ከመሆኑም ሌላ አምላክ በኢየሱስ ደስ እንደሚሰኝ ሲናገር ሰምቷል። በመሆኑም የዮሐንስ እምነት እንደተዳከመ ለማሰብ የሚያበቃ ምክንያት የለንም። እምነቱ ተዳክሞ ቢሆን ኖሮ በዚህ ወቅት ኢየሱስ እሱን አድንቆ ባልተናገረ ነበር። ታዲያ ዮሐንስ ጥርጣሬ ካላደረበት ስለ ኢየሱስ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ለምንድን ነው?

ዮሐንስ፣ ኢየሱስ መሲሕ ስለ መሆኑ ከራሱ ማረጋገጫ ማግኘት ፈልጎ ይሆናል። ይህ በእስር ቤት እየማቀቀ ያለውን ዮሐንስን በጣም ያበረታታዋል። ጥያቄው ሌላም ትርጉም ያለው ይመስላል። አምላክ የቀባው ሰው፣ ንጉሥና አዳኝ እንደሚሆን የሚገልጹትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ዮሐንስ ያውቃል። ይሁንና ኢየሱስ ከተጠመቀ ብዙ ወራት ቢያልፉም ዮሐንስ ከእስር አልተፈታም። በመሆኑም ዮሐንስ፣ መሲሑ እንደሚፈጽማቸው አስቀድሞ በትንቢት የተነገሩትን ነገሮች ሙሉ በሙሉ ለመፈጸም ኢየሱስን ተክቶ የሚመጣ ሌላ ሰው ይመጣ እንደሆነ መጠየቁ ነው።

አንካሳ የነበረ ሰው እንዲሁም ዓይነ ስውር የነበረች ሴት ኢየሱስ ከፈወሳቸው በኋላ ሲደሰቱ

ኢየሱስ ለዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ‘ይመጣል የተባለውማ እኔ ነኝ’ ብሎ ከመመለስ ይልቅ በዚያኑ ሰዓት ብዙዎችን ከሕመምና ከከባድ በሽታ በመፈወስ ከአምላክ የተላከ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሰጣቸው። ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ “ሄዳችሁ የምትሰሙትንና የምታዩትን ነገር ለዮሐንስ ንገሩት፤ ዓይነ ስውሮች እያዩ ነው፤ አንካሶች እየተራመዱ ነው፤ የሥጋ ደዌ የያዛቸው እየነጹ ነው፤ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ ነው፤ ሙታን እየተነሱ ነው፤ ድሆችም ምሥራቹ እየተነገራቸው ነው።”—ማቴዎስ 11:4, 5

የዮሐንስ ጥያቄ፣ ኢየሱስ እያከናወነ ካለው ነገር በተጨማሪ ሌላ ነገር ያደርጋል ብሎ እንደሚጠብቅና ምናልባትም እሱን ከእስር ቤት እንደሚያስፈታው ያስብ እንደነበረ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። ኢየሱስ ግን እየፈጸመው ካለው ተአምራት ሌላ እንዳይጠብቅ ለዮሐንስ መንገሩ ነው።

የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ሲሄዱ ኢየሱስ፣ ዮሐንስ ከነቢያት እንደሚበልጥ ለሕዝቡ ነገራቸው። በሚልክያስ 3:1 ላይ አስቀድሞ የተነገረለት የይሖዋ “መልእክተኛ” እሱ ነው። በሚልክያስ 4:5, 6 ላይ ነቢዩ ኤልያስ ተብሎ የተገለጸውም እሱ ነው። ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከሴት ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም፤ ሆኖም በመንግሥተ ሰማያት ዝቅተኛ የሆነው እንኳ ይበልጠዋል።”—ማቴዎስ 11:11

ኢየሱስ፣ በመንግሥተ ሰማያት ዝቅተኛ የሆነው ዮሐንስን እንደሚበልጠው መናገሩ ዮሐንስ ሰማያዊውን መንግሥት እንደማይወርስ ይጠቁማል። ዮሐንስ ለኢየሱስ መንገዱን ያዘጋጀ ቢሆንም የሞተው ወደ ሰማይ ለመግባት የሚያስችለውን መንገድ ክርስቶስ ከመክፈቱ በፊት ነው። (ዕብራውያን 10:19, 20) ያም ቢሆን ዮሐንስ ታማኝ የአምላክ ነቢይ በመሆኑ የአምላክ መንግሥት ሲገዛ በምድር ላይ ይኖራል።

  • ዮሐንስ “ይመጣል የተባልከው አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” የሚል ጥያቄ ለኢየሱስ ያቀረበው ለምንድን ነው?

  • መጥምቁ ዮሐንስ የትኞቹን ትንቢቶች እንደፈጸመ ኢየሱስ ተናገረ?

  • መጥምቁ ዮሐንስ ከኢየሱስ ጋር በሰማይ የማይሆነው ለምንድን ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ