የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 7 ገጽ 10
  • ትክክለኛ እና አሳማኝ መረጃ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትክክለኛ እና አሳማኝ መረጃ
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ትክክለኛ መረጃ ማስተላለፍ
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ጥቅሶችን ጥሩ አድርጎ ማስተዋወቅ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ጥያቄዎችን መጠቀም
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 7 ገጽ 10

ጥናት 7

ትክክለኛ እና አሳማኝ መረጃ

ጥቅስ

ሉቃስ 1:3

ፍሬ ሐሳብ፦ አድማጮችህ ትክክለኛ መደምደሚያ ላይ እንዲደርሱ ለመርዳት፣ እምነት የሚጣልባቸው መረጃዎችን ተጠቀም።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • አስተማማኝ የመረጃ ምንጮችን ተጠቀም። የምትናገረው ሐሳብ በአምላክ ቃል ላይ የተመሠረተ ይሁን፤ የሚቻል ከሆነ ጥቅሱን በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንብብ። ሳይንሳዊ መረጃ፣ የዜና ዘገባ፣ ተሞክሮ ወይም ሌላ መረጃ የምትጠቅስ ከሆነ ምንጩ አስተማማኝና ጊዜ ያላለፈበት መሆኑን አስቀድመህ አረጋግጥ።

  • የመረጃ ምንጮችን በአግባቡ ተጠቀም። ጥቅሶችን በዙሪያቸው ካለው ሐሳብ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ መልእክት እንዲሁም “ታማኝና ልባም ባሪያ” ካዘጋጃቸው ጽሑፎች ጋር በሚስማማ መንገድ አብራራ። (ማቴ. 24:45) ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑ የመረጃ ምንጮችን የምትጠቅሰው ከጽሑፉ መልእክት ወይም ከጸሐፊው ሐሳብ ጋር በማይጋጭ መልኩ መሆን ይኖርበታል።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    አኃዛዊ ወይም ሌሎች መረጃዎችን አጋንነህ አታቅርብ። “አንዳንድ ሰዎች” የሚለውን “አብዛኞቹ ሰዎች፣” “አንዳንድ ጊዜ” የሚለውን “ሁልጊዜ” እንዲሁም “የሚሆን አይመስልም” የሚለውን “ሊሆን አይችልም” ብለህ እንዳትናገር መጠንቀቅ ይኖርብሃል።

  • መረጃውን መሠረት በማድረግ አስረዳ። አንድ ጥቅስ ካነበብክ ወይም አንድ መረጃ ከጠቀስክ በኋላ አድማጮችህ የራሳቸው መደምደሚያ ላይ እንዲደርሱ ለመርዳት ጥያቄዎችን ጠይቅ አሊያም ነጥቡን በምሳሌ አስረዳ።

ለአገልግሎት

አገልግሎት ከመውጣትህ በፊት፣ ሰዎች ሊያነሱ የሚችሏቸውን ጥያቄዎች አስቀድመህ በማሰብ ምን መልስ እንደምትሰጥ ተዘጋጅ። የምታነጋግረው ሰው መልሱን የማታውቀውን ጥያቄ ቢጠይቅህ በጉዳዩ ላይ ምርምር አድርገህ ሌላ ጊዜ እንደምትመልስለት ልትነግረው ትችላለህ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ