የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 4 ገጽ 7
  • ጥቅሶችን ጥሩ አድርጎ ማስተዋወቅ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጥቅሶችን ጥሩ አድርጎ ማስተዋወቅ
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የጥቅሱን ዓላማ ግልጽ ማድረግ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ጥቅሶችን ጥሩ አድርጎ ማስተዋወቅ
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • የአድማጮችን ልብ ለመንካት መጣር
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ጥሩ መግቢያ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 4 ገጽ 7

ጥናት 4

ጥቅሶችን ጥሩ አድርጎ ማስተዋወቅ

ጥቅስ

ማቴዎስ 22:41-45

ፍሬ ሐሳብ፦ አንድን ጥቅስ ከማንበብህ በፊት አድማጮችህ ለጥቅሱ ጉጉት እንዲያድርባቸው አድርግ።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ጥቅሱን የምታነብበትን ዓላማ ቆም ብለህ አስብ። አድማጮችህ ከጥቅሱ ላይ ልታጎላው የፈለግከውን ነጥብ እንዲያስተውሉ በሚረዳ መንገድ ጥቅሱን አስተዋውቅ።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    በጥቅሱ ዙሪያ ያለውን ሐሳብ ግምት ውስጥ አስገባ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝን ሐሳብ በምትጠቅስበት ጊዜ የተናጋሪውን ወይም የጸሐፊውን ማንነት በትክክል ግለጽ።

  • መጽሐፍ ቅዱስን ዋነኛ ማስረጃ አድርገህ ጥቀስ። በአምላክ መኖር ለሚያምኑ ሰዎች በምትናገርበት ጊዜ የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እርዳቸው፤ ይህን ማድረግህ ከሁሉ የላቀ ጥበብ የያዘውን የአምላክን ቃል እንደምታስተምር ያሳያል።

  • አድማጮችህ ጥቅሱ ምን እንደሚል ለማወቅ እንዲጓጉ አድርግ። ጥያቄ ከጠየቅክ አሊያም አንድ ችግር ከጠቀስክ በኋላ መልሱ ወይም መፍትሔው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደሚገኝ ተናገር፤ አሊያም ደግሞ ለአንድ መሠረታዊ ሥርዓት ምሳሌ የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ጥቀስ።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    አድማጮችህ ስለ ርዕሰ ጉዳዩም ሆነ ስለ ጥቅሱ ምን ያህል እንደሚያውቁ ቆም ብለህ አስብ። የሚያውቁትን ጥቅስም እንኳ ጉጉታቸውን በሚቀሰቅስ መንገድ አስተዋውቅ፤ እንዲሁም ጥቅሱን ከተለየ አቅጣጫ እንዲመለከቱት እርዳቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ