የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 13 ገጽ 16
  • የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥሩ መግቢያ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • የአድማጮችን ልብ ለመንካት መጣር
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • በጋለ ስሜት መናገር
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ግንዛቤ የሚያሰፋ
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 13 ገጽ 16

ጥናት 13

የትምህርቱን ጥቅም ግልጽ ማድረግ

ጥቅስ

ኢሳይያስ 48:17

ፍሬ ሐሳብ፦ አድማጮችህ፣ ትምህርቱ ከሕይወታቸው ጋር እንዴት እንደሚያያዝ እንዲሁም የተማሩትን ነገር እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችሉ እንዲያስተውሉ እርዳቸው።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ስለ አድማጮችህ አስብ። የምታቀርበው ትምህርት ለአድማጮችህ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ ቆም ብለህ አስብ፤ በተለይ እነሱን የሚጠቅማቸው የትኛው ነጥብ እንደሆነ ለማሰብ ሞክር።

  • የትምህርቱን ጠቀሜታ በንግግርህ ላይ ጎላ አድርገህ ግለጽ። ከንግግርህ መጀመሪያ አንስቶ ሁሉም አድማጮች ‘ይህማ ለእኔ ነው’ ብለው እንዲያስቡ በሚያደርግ መንገድ ትምህርቱን አቅርብ። እያንዳንዱን ዋና ነጥብ ስታብራራ፣ ተግባራዊ መሆን የሚችልበትን መንገድም ግለጽ። በደፈናው ከመናገር ይልቅ ነጥቡ ቁልጭ ብሎ እንዲታይ አድርግ።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች የምታብራራበት መንገድ ፍቅር የሚንጸባረቅበትና የአድማጮችህን ስሜት እንደተረዳህ የሚያሳይ ሊሆን ይገባል። የጥፋተኝነት ስሜት እንዲያድርባቸው ከማድረግ ይልቅ ለይሖዋ ያላቸውን ፍቅርና እምነታቸውን ለማጠናከር ጥረት አድርግ፤ አድማጮችህ ትክክል የሆነውን ነገር የማድረግ ልባዊ ፍላጎት እንዳላቸው እንደምትተማመን በሚያሳይ መንገድ ንግግርህን አቅርብ።

ለአገልግሎት

በስብከቱ ሥራ ላይ የምትጠቀምበትን መግቢያ ስትዘጋጅ፣ ወቅታዊ የዜና ዘገባዎችን እንዲሁም በክልልህ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ ጉዳዮችን በመግቢያህ ውስጥ ለማካተት ሞክር። ሰዎችን ስታነጋግር በወቅቱ እያሳሰባቸው ባለው ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርግ። የምታነጋግረው ግለሰብ የሚያሳስበው ነገር ምን እንደሆነ ለማወቅ፣ ቅር በማያሰኝ መንገድ ጥያቄዎችን አቅርብለት። የሚሰጠውን ምላሽ ካዳመጥክ በኋላ የምትናገረውን ነገር እንደሁኔታው ማስተካከል ትችላለህ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ