የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 11/15 ገጽ 13
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ብሉይ ኪዳን” ምን ያህል ተዓማኒነት አለው?
    መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?
  • እየመራን ባለው በክርስቶስ ላይ እምነት ይኑራችሁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የኢያሪኮ ግንብ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 11/15 ገጽ 13
ካህናት ቀንደ መለከት ሲነፉና ኢያሱ የጦርነት ጩኸት ሲያሰማ፤ ከዚያም የኢያሪኮ ግንብ መፍረስ ሲጀምር

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የጥንቷ ኢያሪኮ ድል የተደረገችው ለረጅም ጊዜ ሳትከበብ ለመሆኑ ምን ማስረጃ አለ?

በኢያሱ 6:10-15, 20 መሠረት የእስራኤል ሠራዊት ኢያሪኮን ለስድስት ቀናት፣ በቀን አንድ ጊዜ ይዞራት ነበር። በሰባተኛው ቀን ግን ሠራዊቱ ከተማዋን ሰባት ጊዜ የዞራት ሲሆን አምላክም ግዙፍ የሆነው የኢያሪኮ ቅጥር እንዲፈርስ አድርጓል። ይህም እስራኤላውያን ወደ ኢያሪኮ ገብተው ድል እንዲያደርጓት አስችሏቸዋል። ታዲያ ኢያሪኮ ተከባ የቆየችው ለአጭር ጊዜ እንደሆነ የሚገልጸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ አርኪኦሎጂያዊ ግኝቶች ያረጋግጣሉ?

በጥንት ዘመን ወራሪዎች በግንብ የታጠረችን ከተማ ለማጥቃት ዙሪያዋን መክበባቸው የተለመደ ነበር። ወራሪዎቹ የከበቧትን ከተማ ድል አድርገው ለመቆጣጠር የሚፈጅባቸው ጊዜ ምንም ያህል ይሁን፣ በከተማዋ ውስጥ የተረፈውን እህል ጨምሮ የከተማዋን ሀብት በሙሉ ይመዘብራሉ። ይሁን እንጂ የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎች የኢያሪኮን ፍርስራሽ ሲመረምሩ ከፍተኛ የእህል ክምችት አግኝተዋል። ቢብሊካል አርኪኦሎጂ ሪቪው የተሰኘ መጽሔት ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ ይላል፦ “በከተማዋ ፍርስራሽ ውስጥ ከሸክላ ዕቃዎች ሌላ በብዛት የተገኘው ነገር እህል ነው። . . . በፓለስቲና ምድር በተደረገው አርኪኦሎጂያዊ ምርምር ይህ ያልተለመደ ነገር ነው። [በቁፋሮ ወቅት] አንድ ወይም ሁለት ጎታ እህል ይገኝ ይሆናል፤ ይህን ያህል ብዛት ያለው እህል ማግኘት ግን አዲስ ነገር ነው።”

ቅዱስ ጽሑፋዊው ዘገባ በሚናገረው መሠረት እስራኤላውያን የኢያሪኮን እህል ያልዘረፉበት በቂ ምክንያት ነበራቸው። ይሖዋ ምንም ነገር እንዳይወስዱ አዟቸው ነበር። (ኢያሱ 6:17, 18) እስራኤላውያን ኢያሪኮን የወረሯት የመከር ወቅት እንዳለፈ በመሆኑ ከተማዋ ከፍተኛ የእህል ክምችት ነበራት። (ኢያሱ 3:15-17፤ 5:10) በኢያሪኮ ውስጥ ብዙ እህል መገኘቱ፣ እስራኤላውያን ከተማዋን የከበቧት ልክ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገልጸው ለአጭር ጊዜ እንደሆነ ይጠቁማል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ