የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 10 ገጽ 13
  • ድምፅን መለዋወጥ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ድምፅን መለዋወጥ
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ድምፅን መለዋወጥ
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ማጥበቅና ድምፅን መለዋወጥ
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • ተስማሚ የድምፅ መጠን
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • በጋለ ስሜት መናገር
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 10 ገጽ 13

ጥናት 10

ድምፅን መለዋወጥ

ጥቅስ

ምሳሌ 8:4, 7

ፍሬ ሐሳብ፦ የድምፅህን መጠን፣ ውፍረትና ቅጥነት እንዲሁም የምትናገርበትን ፍጥነት በመለዋወጥ መልእክቱን በግልጽ ለማስተላለፍ ብሎም የአድማጮችህን ስሜት ለመቀስቀስ ጥረት አድርግ።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • የድምፅን መጠን መለዋወጥ። የድምፅህን መጠን ከፍ በማድረግ ዋና ዋና ነጥቦችን ማጉላትና አድማጮችህን ለተግባር ማነሳሳት ትችላለህ። የፍርድ መልእክት የያዙ ቅዱስ ጽሑፋዊ ሐሳቦችን ስታነብም እንዲሁ አድርግ። አድማጮችህ ጉጉት እንዲያድርባቸው ለማድረግ ዝግ ባለ ድምፅ ተናገር፤ የፍርሃትና የጭንቀት ስሜት የሚንጸባረቅበት ሐሳብ በምትናገርበት ጊዜም በዚህ ዘዴ መጠቀም ትችላለህ።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    በተደጋጋሚ ድምፅህን ከፍ እያደረግክ የምትናገር ከሆነ አድማጮችህ እየወቀስካቸው እንዳለ ሊሰማቸው ይችላል። ድምፅህን የምትለዋውጠው በተጋነነ መንገድ መሆን የለበትም፤ አለዚያ አድማጮችህ ትምህርቱን ትተው በአንተ ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይችላሉ።

  • የድምፅን ውፍረትና ቅጥነት መለዋወጥ። ሞቅ ባለ ስሜት ለመናገር አሊያም መጠንን ወይም ርቀትን ለመግለጽ ድምፅህን ቀጠን ማድረግ ትችላለህ፤ እርግጥ እንዲህ ያለውን የአነጋገር ዘዴ የምትጠቀመው በአካባቢህ የተለመደ ከሆነ ነው። የሐዘን ወይም የጭንቀት ስሜትን ለማንጸባረቅ ደግሞ ወፈር ባለ ድምፅ ተናገር።

  • የምትናገርበትን ፍጥነት መለዋወጥ። ለየት ያለ ስሜት (ደስታ፣ ድንጋጤ ወዘተ) የሚፈጥር ነገር ስትናገር ፍጥነትህን ጨመር አድርግ። አስፈላጊ የሆኑ ነጥቦችን ስትጠቅስ ደግሞ ረጋ ብለህ ተናገር።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    አድማጮችህ ግራ እንዳይጋቡ በድንገት የድምፅህን ፍጥነት አትጨምር። በተጨማሪም የምትናገራቸውን ቃላት አጥርቶ ለመስማት እስኪያስቸግር ድረስ መፍጠን አይኖርብህም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ