የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ጥናት 8 ገጽ 11
  • ትምህርት አዘል ምሳሌዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትምህርት አዘል ምሳሌዎች
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ተስማሚ ምሳሌዎች
    ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መመሪያ መጽሐፍ
  • “ያለምሳሌ አይነግራቸውም ነበር”
    “ተከታዬ ሁን”
  • “ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • በጥልቅ ማስተዋልና በማሳመን ችሎታ ተጠቅማችሁ አስተምሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ጥናት 8 ገጽ 11

ጥናት 8

ትምህርት አዘል ምሳሌዎች

ጥቅስ

ማቴዎስ 13:34, 35

ፍሬ ሐሳብ፦ የአድማጮችህን ትኩረት የሚስቡና ዋናውን ነጥብ ለማጉላት የሚረዱ ቀለል ያሉ ምሳሌዎችን በመጠቀም ንግግርህ ማራኪ እንዲሆን ማድረግ ትችላለህ።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ቀላል የሆኑ ምሳሌዎችን ተጠቀም። ኢየሱስ እንዳደረገው ቀላል ምሳሌዎችን በመጠቀም ከባድ ወይም ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮችን ማስረዳት ትችላለህ። ምሳሌውን የሚያወሳስቡ አላስፈላጊ ዝርዝር ነጥቦችን አትጥቀስ። የምትጠቀምበት ምሳሌ ከትምህርቱ ጋር የሚጣጣም ሊሆን ይገባል፤ ምሳሌው ከነጥቡ ጋር እንዴት እንደሚያያዝ ግልጽ ካልሆነ አድማጮችህ ግራ ሊጋቡ ይችላሉ።

    ጠቃሚ ሐሳብ

    አስተዋይ ሁን። በአካባቢህ ለሚከናወኑ ነገሮች ትኩረት ስጥ፤ ጽሑፎቻችንን በሚገባ አንብብ፤ እንዲሁም ጥሩ ተናጋሪዎችን ልብ ብለህ ተከታተል። ይህን ማድረግህ፣ ስታስተምር ልትጠቀምባቸው የምትችላቸውን ምሳሌዎች ለማግኘት ይረዳሃል። እነዚህን ምሳሌዎች ሰብስበህ በፋይል አስቀምጣቸው።

  • ስለ አድማጮችህ አስብ። ከአድማጮችህ ሕይወት ጋር የተያያዙና ትኩረታቸውን ሊስቡ የሚችሉ ምሳሌዎች ተጠቀም። አድማጮችህን የሚያሸማቅቁ ወይም ቅር የሚያሰኙ ምሳሌዎች አትጠቀም።

  • ዋናው ነጥብ ላይ ትኩረት አድርግ። ምሳሌህ ዝርዝር ሐሳቦችን ሳይሆን ዋናውን ነጥብ የሚያጎላ ሊሆን ይገባል። አድማጮችህ ምሳሌውን ብቻ ሳይሆን ከምሳሌው የሚገኘውን ትምህርትም እንዲያስታውሱ እርዳቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ