የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 7/15 ገጽ 32
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ደኖች
    ንቁ!—2023
  • አሞጽ የባሉጥ ፍሬ ለቃሚ ወይስ ወጊ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • “በምድር ላይ በትልቅነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ሕይወት ያለው በራሪ ማሽን”
    ንቁ!—2010
  • እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ይቀመጣል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 7/15 ገጽ 32
በገሊላ የሚገኘው የቢሪያ ደን

በገሊላ የሚገኘው የቢሪያ ደን

ይህን ያውቁ ኖሯል?

የጥንቷ እስራኤል መጽሐፍ ቅዱስ የሚገልጸውን ያህል በደን የተሸፈነች ነበረች?

የተስፋይቱ ምድር አንዳንድ አካባቢዎች በደን የተሸፈኑና ዛፎች ‘በብዛት’ የሚገኙባቸው እንደነበሩ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (1 ነገ. 10:27፤ ኢያሱ 17:15, 18) ሆኖም በዛሬው ጊዜ አብዛኛው የአገሪቱ ክፍል የተመነጠረ ከመሆኑ አንጻር አንዳንዶች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰው ሐሳብ እውነት መሆኑን ይጠራጠሩ ይሆናል።

እጅብ ብለው የበቀሉ የሾላ ፍሬዎች

እጅብ ብለው የበቀሉ የሾላ ፍሬዎች

ላይፍ ኢን ቢብሊካል ኢዝሬል የተሰኘው መጽሐፍ “በጥንቷ እስራኤል፣ በዛሬው ጊዜ ካለው እጅግ የሚበልጥ ሰፊ ቦታ የሚሸፍኑ ደኖች ነበሩ” ይላል። በደጋ አካባቢ የሚገኘው የተፈጥሮ ደን በዋነኝነት ጥድን (Pinus halepensis)፣ ባሉጥን (Quercus calliprinos) እና ቴረቢንዝን (Pistacia palaestina) ያካትት ነበር። በማዕከላዊው የተራራ ሰንሰለትና በሜድትራንያን የባሕር ዳርቻ መካከል ያለውን አካባቢ በሚጨምረው በሸፌላ ደግሞ የሾላ ዛፎችም (Ficus sycomorus) በብዛት ይገኙ ነበር።

ፕላንትስ ኦቭ ዘ ባይብል የተሰኘው መጽሐፍ በአሁኑ ጊዜ በእስራኤል አንዳንድ አካባቢዎች ዛፍ የሚባል ነገር እንደሌለባቸው ይናገራል። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው? ይህ ቀስ በቀስ የተከሰተ ነገር እንደሆነ መጽሐፉ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦ “ሰዎች በዋነኝነት የእርሻና የግጦሽ ቦታቸውን ለማስፋት እንዲሁም ለግንባታ ቁሳቁሶችና ለማገዶ የሚሆን እንጨት ለማግኘት ሲሉ የተፈጥሮውን ደን ለረጅም ጊዜ ሲጨፈጭፉት ቆይተዋል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ