የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • rr ገጽ 212
  • የምድሪቱ አከፋፈል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የምድሪቱ አከፋፈል
  • የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የተረጋገጠ ቦታና ትልቅ ግምት የሚሰጠው የሥራ ድርሻ
  • እኩል ድርሻ
  • ‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ ተከፋፈሉ’
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
  • በአምላክ ቤተ መቅደስ ላይ “ልብህን አድርግ”!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • “ከተማዋ ‘ይሖዋ በዚያ አለ’ ተብላ ትጠራለች”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
  • “ቤተ መቅደሱ” እና “አለቃው” በዛሬው ጊዜ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
rr ገጽ 212
መዳብ የሚመስል መልክ ያለው ሰው ለሕዝቅኤል ርስቶቹን ሲያሳየው።

ሣጥን 20ሀ

የምድሪቱ አከፋፈል

የምድሪቱ ወሰኖች ልኬት በዝርዝር መገለጹ ግዞተኞቹ የሚወዷት አገራቸው ተመልሳ እንደምትቋቋም እርግጠኛ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ዛሬስ ከዚህ ራእይ ምን ትምህርት እናገኛለን? የራእዩን ሁለት ገጽታዎች እስቲ እንመልከት፦

ሕዝቅኤል በጻፈው መሠረት፣ ከግዞት ለተመለሱት እስራኤላውያን የሚከፋፈለውን ርስት የሚያሳይ ካርታ። ለነገዶቹ የተሰጠው መሬት ከሰሜን እስከ ደቡብ በሚከተለው ቅደም ተከተል እኩል ቦታ ተከፋፍሏል፦ ዳን፣ አሴር፣ ንፍታሌም፣ ምናሴ፣ ኤፍሬም፣ ሮቤል፣ ይሁዳ፣ በመዋጮ የተሰጠው መሬት (የአስተዳደር ማዕከል)፣ ቢንያም፣ ስምዖን፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን እና ጋድ።

የተረጋገጠ ቦታና ትልቅ ግምት የሚሰጠው የሥራ ድርሻ

ራእዩ ከግዞት የሚመለሱት እስራኤላውያን በሙሉ ተመልሳ በምትቋቋመው ተስፋይቱ ምድር ውስጥ ርስት እንደሚያገኙ ያመለክት ነበር። ዛሬም በተመሳሳይ ሁሉም የይሖዋ አገልጋዮች በመንፈሳዊው ገነት ውስጥ ቦታ አላቸው። በድርጅቱ ውስጥ የምናበረክተው አስተዋጽኦ ምንም ያህል አነስተኛ ቢሆን፣ በመንፈሳዊው ገነት ውስጥ የተረጋገጠ ቦታና ከፍ ያለ ግምት የሚሰጠው የሥራ ድርሻ አለን። ሁሉም የይሖዋ አገልጋዮች በእሱ ፊት በእኩል ደረጃ ውድ ናቸው።

እኩል ድርሻ

በሕዝቅኤል ራእይ መሠረት፣ በሁሉም ነገዶች ርስት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ምድሪቱ ከምታስገኘው የተትረፈረፈ ምርት በእኩል መጠን ተጠቃሚዎች ይሆናሉ። ዛሬም በተመሳሳይ ይሖዋ አገልጋዮቹ በሙሉ መንፈሳዊው ገነት ከሚያስገኛቸው በረከቶች በእኩል ደረጃ ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።

ወደ ምዕራፍ 20 ከአንቀጽ 5-11 ተመለስ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ