መዝሙር 8
ይሖዋ መጠጊያችን ነው
በወረቀት የሚታተመው
(መዝሙር 91)
1. ይሖዋ መጠጊያችን፤
ጽኑ መከታችን።
እንኑር ተረጋግተን፤
በጥላው ሥር ሆነን።
ታማኞቹን ይታደጋል፤
እናውቃለን ያድነናል።
ታማኝ ነው አምላካችን፤
ይሆናል መሸሸጊያችን።
2. ጎናችን ሺ ቢወድቁም፣
ብዙ ሰዎች ቢያልቁም፣
ቅኖች ግን ይድናሉ፤
ጻድቃን ይተርፋሉ።
ጥፋት እኛ ጋ አይቀርብም፤
አንፈራም፣ አንሸበርም።
አምላክ ይጠብቀናል፤
በክንፉም ይከልለናል።
3. በመንገድ ካለ ወጥመድ፣
አምላክ ያድነናል።
ፍላጻው አይጎዳንም፤
ጥፋት አይነካንም።
የሚያስፈራን ነገር የለም፤
ምንም አያሸብረንም።
ይሖዋ መጠጊያችን፤
የዘላለም ጠባቂያችን።
(በተጨማሪም መዝ. 97:10፤ 121:3, 5ን እና ኢሳ. 52:12ን ተመልከት።)