መዝሙር 107
መለኮታዊው የፍቅር መንገድ
በወረቀት የሚታተመው
1. ከአምላክ ተማርን እውነተኛ ፍቅርን፤
በተግባር አሳየን።
ከሥራዎቹ አየን ታላቅ ፍቅሩን፣
ባሕርያቱን፣ ማንነቱን።
ነፃ ሊያወጣን ከኃጢያት ባርነት
ልጁን ላከልን፤ አሳየን ጥሩነት፤
በዚ’ም አውቀናል የሱን ፍቅር ጥልቀት።
እንምሰለው፤ አምላክ ፍቅር ነው።
2. በአምላክ መንገድ ከሄድን ፍቅራችን
የእውነት ይሆናል።
አድሎ ሳናደርግ ወንድሞቻችንን
እንርዳቸው ከልባችን።
አምላክንና ወንድሞችን መውደድ
ያስፈልገናል፤ ይጠበቅብናል።
ሌሎችን ይቅር ማለት ያስችለናል።
ይታይ ፍቅር፤ ልባዊ ፍቅር።
3. አስተሳስሮናል እውነተኛ ፍቅር፤
ቤተሰብ አ’ርጎናል።
አምላካችንም በፍቅር ጋብዞናል፤
ከሕዝቡ ጋር አንድ ሆነናል።
ልባዊ ፍቅር መለያችን ሆኗል፤
አምላክ በቃሉ ሕዝቦቹን ይመራል።
የሚያስቡልን ወንድሞች ሰጥቶናል።
’ናመስግነው፤ አምላክ ፍቅር ነው።