መዝሙር 43
የምስጋና ጸሎት
በወረቀት የሚታተመው
1. አባት ሆይ፣ በጸሎት ቀርበናል ፊትህ፤
ልናመሰግን፣ ልናወድስህ።
አንተን ስናገለግል እምነት አለን፤
እንደምትደግፈን እናውቃለን።
ብዙ ነው በደል፣ መተላለፋችን፤
’ባክህ ይቅር በል ድካማችንን።
ለሰጠኸን ቤዛ አመስጋኞች ነን፤
ከኃጢያት፣ ከሞት ስለዋጀኸን።
2. ወዳንተ የጠራኸን አምላካችን
ለደግነትህ እናመስግንህ።
እርዳን በመንገድህ ላይ እንድንጓዝ፣
ለዘላለም አንተን ’ንድናመልክህ።
ቅዱስ መንፈስህን ስለምትሰጠን
ያንተን ግርማ ሁሌ ’ናውጃለን።
እናገለግልሃለን በደስታ፤
ሕዝብህን ስለምታበረታ።