የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • sjj መዝ. 139
  • በአዲሱ ዓለም ስትኖር ይታይህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በአዲሱ ዓለም ስትኖር ይታይህ
  • ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በአዲሱ ዓለም ስትኖር ይታይህ
    ለይሖዋ ዘምሩ
  • የመንግሥቱን መዝሙር ዘምሩ!
    ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
  • የመንግሥቱን መዝሙር ዘምሩ!
    ለይሖዋ ዘምሩ
  • ለይሖዋ ክብር ስጡ
    ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
ለተጨማሪ መረጃ
ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
sjj መዝ. 139

መዝሙር 139

በአዲሱ ዓለም ስትኖር ይታይህ

በወረቀት የሚታተመው

(ራእይ 21:1-5)

  1. 1. እኔም አንተም፣ ሁላችንም፣

    ይታይህ ስንኖር ባዲስ ዓለም።

    ነፃ መሆን፣ ሰላም ማግኘት

    አቤት እንዴት እንደሚያስደስት!

    ያምላክ መንግሥት እንከን የለው፤

    ጨርሶ አይኖርም ክፉ ሰው።

    ጊዜው ደርሷል ባዲስ ዓለም ለመኖር፤

    ያብቃን ከልባችን

    ላምላክ ለመዘመር፦

    (አዝማች)

    “አምላካችን ሆይ፣ እናመስግንህ፤

    ሁሉን ነገር አዲስ በማድረግህ።

    እንዘምር በደስታ እናቅርብ ምስጋና፣

    ውዳሴና ክብር ’ሚገባህ ነህና።”

  2. 2. እኔም አንተም፣ ባዲስ ዓለም፣

    ይታይህ ስንኖር ለዘላለም።

    የምናየው፣ የምንሰማው

    አያስፈራም፤ አያሰጋንም።

    ይፈጸማል የአምላክ ቃል፤

    ድንኳኑም ከኛ ጋር ይሆናል።

    በሞት ያንቀላፉትንም ያስነሳል፤

    እነሱም ከኛ

    ጋር ያመሰግኑታል፦

    (አዝማች)

    “አምላካችን ሆይ፣ እናመስግንህ፤

    ሁሉን ነገር አዲስ በማድረግህ።

    እንዘምር በደስታ እናቅርብ ምስጋና፣

    ውዳሴና ክብር ’ሚገባህ ነህና።”

(በተጨማሪም መዝ. 37:10, 11⁠ን፣ ኢሳ. 65:17⁠ን፣ ዮሐ. 5:28⁠ን እና 2 ጴጥ. 3:13⁠ን ተመልከት።)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ