ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ ሁለተኛው ደብዳቤ የመጽሐፉ ይዘት 1 ሰላምታ (1, 2) አምላክ በመከራ ሁሉ ያጽናናናል (3-11) ጳውሎስ የጉዞ ዕቅዱን ለወጠ (12-24) 2 ጳውሎስ የጉባኤውን አባላት ለማስደሰት የነበረው ፍላጎት (1-4) ይቅር የተባለና የተመለሰ ኃጢአተኛ (5-11) ጳውሎስ በጥሮአስና በመቄዶንያ (12, 13) አገልግሎት፣ የድል ሰልፍ (14-17) “የአምላክን ቃል አንሸቃቅጥም” (17) 3 “የምሥክር ወረቀት” (1-3) “የአዲስ ቃል ኪዳን አገልጋዮች” (4-6) አዲሱ ቃል ኪዳን ያለው የላቀ ክብር (7-18) 4 የምሥራቹ ብርሃን (1-6) “የማያምኑትን ሰዎች አእምሮ አሳውሯል” (4) በሸክላ ዕቃ ውስጥ ያለ ውድ ሀብት (7-18) 5 ‘ከሰማይ የሆነውን መኖሪያ መልበስ’ (1-10) “የማስታረቅ አገልግሎት” (11-21) “አዲስ ፍጥረት” (17) የክርስቶስ አምባሳደሮች (20) 6 የአምላክን ጸጋ አላግባብ መጠቀም አይገባም (1, 2) ስለ ጳውሎስ አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ (3-13) “አቻ ባልሆነ መንገድ አትጠመዱ” (14-18) 7 “ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ” (1) ጳውሎስ በቆሮንቶስ ክርስቲያኖች የተነሳ የተሰማው ደስታ (2-4) ቲቶ ጥሩ ዜና ይዞ መጣ (5-7) አምላካዊ ሐዘንና ንስሐ መግባት (8-16) 8 ለአይሁዳውያን ክርስቲያኖች መዋጮ ማሰባሰብ (1-15) ቲቶን ወደ ቆሮንቶስ ለመላክ ታሰበ (16-24) 9 ለጋሶች እንዲሆኑ የተሰጠ ማበረታቻ (1-15) ‘አምላክ በደስታ የሚሰጠውን ይወዳል’ (7) 10 ጳውሎስ ስለ አገልግሎቱ ተሟገተ (1-18) “የጦር መሣሪያዎቻችን ሥጋዊ አይደሉም” (4, 5) 11 ጳውሎስና ምርጦቹ ሐዋርያት (1-15) ጳውሎስ ሐዋርያ ሆኖ ሲያገለግል ያጋጠሙት መከራዎች (16-33) 12 ጳውሎስ ያያቸው ራእዮች (1-7ሀ) “ሥጋዬን የሚወጋ እሾህ ተሰጠኝ” (7ለ-10) ከምርጦቹ ሐዋርያት አላንስም (11-13) ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ያሳየው አሳቢነት (14-21) 13 መጨረሻ ላይ የሰጠው ማስጠንቀቂያና ማሳሰቢያ (1-14) ‘በእምነት ውስጥ መሆናችሁን ለማረጋገጥ ራሳችሁን ፈትሹ’ (5) ‘መስተካከላችሁንና በሐሳብ መስማማታችሁን ቀጥሉ’ (11)