የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g04 5/8 ገጽ 32
  • የሕፃናት የመማር ችሎታ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሕፃናት የመማር ችሎታ
  • ንቁ!—2004
ንቁ!—2004
g04 5/8 ገጽ 32

የሕፃናት የመማር ችሎታ

ብዙውን ጊዜ አዋቂዎች ሕፃናት ምን ያህል መማር እንደሚችሉ አይገነዘቡም። ሆኖም አብዛኛውን ጊዜ ልጆች አዲስ ቋንቋ በመማር ረገድ ከወላጆቻቸው ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። አንዳንድ ልጆች በአራት ዓመት ዕድሜያቸው ሁለትና ከዚያም በላይ ቋንቋዎችን መናገር ይችላሉ። በኦበርን፣ ዋሽንግተን፣ ዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር ራንዳ የተባለች አንዲት ሴት ይህን ሐቅ መቀበል ከብዷት ነበር። ባለፈው ዓመት በጻፈችው ደብዳቤ ላይ “በጣም እንደተሳሳትኩ እንድገነዘብ ስለረዳችሁኝ አመሰግናለሁ” ብላለች።

ራንዳ በነሐሴ 1, 1988 መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጣ አንድ ተሞክሮ እንዳነበበች ትናገራለች። “መጽሔቱ በገጽ 13 ላይ አራት ዓመት ተኩል የሆነው ልጅ ስላላት አንዲት እናት ይናገራል፤ ይህቺ እናት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባለውን መጽሐፍ ለልጅዋ እያነበበችለት እያለ በመሃል ቆም ስትል ልጁ ከአፏ ቀበል አድርጐ አንድም ሳይሳሳት ታሪኩን እንደተናገረ ገልጻለች። ለመያዝ አስቸጋሪ የሆኑ የቦታና የሰዎች ስሞችን ጨምሮ የመጽሐፉን 33 ምዕራፎች በቃሉ እንደያዛቸው አክላ ተናግራለች። በወቅቱ ይህ የማይሆን ነገር ነው ብዬ እንዳሰብኩ አልክድም። ሆኖም ተሳስቼ ነበር። አሁን እኔ ራሴ አራት ዓመት የሆናት ሴት ልጅ ያለችኝ ሲሆን በዚህ መጽሐፍ ላይ ያሉትን አብዛኞቹን ታሪኮች በቃሏ ይዛቸዋለች።”

ልጅዎን ለማስተማር ምን ያደረጉት ነገር አለ? የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባለው ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ እንዲላክልዎት መጠየቅ ይችላሉ። ይህ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተገለጹ ሰዎችና ክንውኖች የሚገልጹ 116 ታሪኮችን ይዟል። ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ከሞሉ በኋላ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

□ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባለውን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ማግኘት እችላለሁ?

□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ