የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 8/07 ገጽ 5
  • ሥልጣናችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሥልጣናችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት
  • ንቁ!—2007
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እናንት ወላጆች፣ ልጆቻችሁን በፍቅር አሠልጥኗቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ለሥልጣን አክብሮት ማሳየት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • በመንፈሳዊ ጠንካራ የሆነ ቤተሰብ መገንባት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ወላጆች፣ ልጆቻችሁ ይሖዋን እንዲወዱ እርዷቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2007
g 8/07 ገጽ 5

3

ሥልጣናችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ጥናቶች እንዳሳዩት “ወላጆቻቸው በጣም ልል ወይም ከመጠን በላይ ጥብቅ ከሆኑ ልጆች ይልቅ አፍቃሪ የሆኑና ልጆቹ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ የሚሰጡ ሆኖም በሥልጣናቸው በአግባቡ የሚጠቀሙ እንዲሁም ጥብቅ ገደብ የሚያወጡ ወላጆች ያሳደጓቸው ልጆች፣ በጥቅሉ ሲታይ በትምህርት ጥሩ ውጤት ያመጣሉ፤ በማኅበራዊ ግንኙነት ረገድም የተሻሉ ናቸው፤ ለራሳቸው ጥሩ ግምት አላቸው እንዲሁም ደስተኞች ናቸው” በማለት ፓረንትስ የተባለው መጽሔት ዘግቧል።

ተፈታታኝ የሚሆነው ለምንድን ነው? ልጆች ከሕፃንነታቸው አንስቶ ወደ አሥራዎቹ ዕድሜ እስኪገቡ ድረስ በእነሱ ላይ ያላችሁን ሥልጣን ለመቀበል ያንገራግራሉ። ፓረንት ፓወር! የተሰኘው መጽሐፍ ደራሲ የሆኑት ጆን ሮዝሞንድ “ወላጆች በሥልጣናቸው ለመጠቀም ፈርተው ለልጆቹ ፍላጎት በቀላሉ የመሸነፍ አዝማሚያ ካላቸው ልጆች ይህን ማስተዋል አይከብዳቸውም” በማለት ጽፈዋል። ደራሲው አክለውም “‘አዛዡ ማን ነው?’ የሚለው ጥያቄ ሲነሳ ወላጆች ሥልጣናቸውን ካልተጠቀሙበት ልጆች አዛዥ ይሆናሉ” ብለዋል።

መፍትሔው ምንድን ነው? የወላጅነት ሥልጣናችሁን በመጠቀም ልጆቻችሁ እንዲታዘዟችሁ ብታደርጉ ልጆቹ እንደሚርቋችሁ ወይም መንፈሳቸው እንደሚደቆስ በማሰብ አትጨነቁ። የቤተሰብ መሥራች የሆነው ይሖዋ አምላክ ቤተሰብን በማስተዳደር ረገድ ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር እኩል ሥልጣን እንዲኖራቸው ዓላማው አይደለም። ከዚህ ይልቅ ለወላጆች ቤተሰቡን የመምራት ሥልጣን የሰጣቸው ሲሆን ልጆችን ደግሞ “ለወላጆቻችሁ . . . ታዘዙ” ብሎ አዟቸዋል።—ኤፌሶን 3:14, 15፤ 6:1-4

እናንተም አምባገነን ሳትሆኑ በሥልጣናችሁ መጠቀም ትችላላችሁ። እንዴት? የይሖዋን ምሳሌ በመከተል ነው። ይሖዋ ሰብዓዊ ልጆቹ ፈቃዱን እንዲያደርጉ ማስገደድ ቢችልም እንዲህ በማድረግ ፋንታ፣ ባሏቸው መልካም ባሕርያት ተገፋፍተው እንዲታዘዙት ያበረታታቸዋል። የአምላክ ቃል “ትእዛዜን ሰምተህ ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ ሰላምህ እንደ ወንዝ . . . በሆነ ነበር” ይላል። (ኢሳይያስ 48:18) ይሖዋ በፍርሃት እየተርበደበድን ሳይሆን በፍቅር እንድንታዘዘው ይፈልጋል። (1 ዮሐንስ 5:3) ይሖዋ ከእኛ በሚፈልገው ነገር ረገድ ምክንያታዊ ከመሆኑም ሌላ የሥነ ምግባር መሥፈርቶቹን ጠብቀን ከኖርን እንደምንጠቀምም ያውቃል።—መዝሙር 19:7-11

የወላጅነት ሥልጣናችሁን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችላችሁን በራስ የመተማመን መንፈስ ማዳበር የምትችሉት እንዴት ነው? በመጀመሪያ ደረጃ፣ አምላክ እንዲህ እንድታደርጉ እንደሚጠብቅባችሁ ማመን ያስፈልጋችኋል። ሁለተኛ፣ እናንተም ሆናችሁ ልጆቻችሁ በአምላክ የሥነ ምግባር መሥፈርቶች መሠረት መኖራችሁ የተሻለ ሕይወት እንድትመሩ እንደሚያስችላችሁ ልታምኑ ይገባል።—ሮሜ 12:2

ሥልጣናችሁን በአግባቡ ለመጠቀም በተለይ ምን ማድረግ አለባችሁ?

[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

“ልጅህን ቅጣው፤ . . . ነፍስህንም ደስ ያሰኛታል።”—ምሳሌ 29:17

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ